በአፈ/ከሣሽ አቶ ብዙአየሁ አለማየሁ እና በአፈ/ተከሣሽ አቶ ዮሴፍ ካሰኝ መካከል ስለአለው የአፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ የፍርድ ባለዕዳ ንብረት የሆነው ኮድ አ.አ- 02-C13196 ተሽከርካሪ መኪና በጨረታ እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ አዟል፡፡ ስለሆነም በጨረታ ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።
የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በአፈ/ከሣሽ አቶ ብዙአየሁ አለማየሁ እና በአፈ/ተከሣሽ አቶ ዮሴፍ ካሰኝ መካከል ስለአለው የአፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ የፍርድ ባለዕዳ ንብረት የሆነው ኮድ አ.አ- 02-C13196 ተሽከርካሪ መኪና መነሻ ዋጋ 1,915,884.85 /አንድ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ አስራ አምስት ሺህ ስምስት መቶ ሰማኒያ አራት ብር ከሰማኒያ አምስት ሣንቲም/ ንብረቱ በሚገኝበት በእምዬ ምኒሊክ ክ/ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት ግቢ ጥር 17 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት በጨረታ እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ አዟል፡፡
በመሆኑም ፡-
- ገዥው /ተጫራቹ / የመኪናውን የግምቱን 1/4ኛ ገንዘብ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወዲያውኑ ለሀራጅ ባዩ የማስያዝ ግዴታ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
- ንብረቱን ለመሸጥ ምክንያት የሆነው ለፍርድ ማስፈፀሚያ ነው፡፡
- ገዥው በጨረታ ለገዛው ንብረት ዋጋውን ሣይከፍል የቀረ እንደሆነ ወይም በህግ በተወሰነው በዚሁ የሽያጭ ማስታወቂያ ላይ በተገለፀው መሠረት ዋጋውን ያላስቀመጠ እንደሆነ ሽያጩ ይሠረዛል፤ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/429/2/ መሠረት ለሃራጅ ማስታወቂያው የተደረገውን ወጪ እንዲከፍል ይገደዳል፡፡
- የሐራጅ ማስታወቂያውን ለማቋረጥ የሚቻልበት የተሻለ መንገድ ካለ የጨረታ ማስታወቂያው በማንኛውም ጊዜ ሊቋረጥ ይችላል፡፡
የሰ/ሸዋ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት
ደ/ብርሃን
