Tender Detail

Tender Details

  • Company የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት
  • Address አሶሳ ከተማ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና ካብኔ ጉዳዮች ጽ/ቤት ግዢና ንብረት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 104 : ደቡብ ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 09 21-17-78-90
  • Website
  • Deadline15 Jan 2025, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Vehicle tire

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት በ2017 ዓ.ም ቢያዘው እቅድ መሰረት ሎት 1 ለጽ/ቤቱ ተሽከርካሪ መኪናዎች አገልግሎት የሚውል የቀላል መኪና ጎማዎች ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት በ2017 ዓ.ም ቢያዘው እቅድ መሰረት ሎት 1 ለጽ/ቤቱ ተሽከርካሪ መኪናዎች አገልግሎት የሚውል የቀላል መኪና ጎማዎች ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ተጫራቾች ፤

  1. በግልጽ ጨረታ ዋጋ ማቅረቢያቸው ላይ የድረጅታቸውን ስምና አድራሻቸውን ስልጣን በተሰጠው የድርጅቱ ኃላፊ ተፈርሞ እና ህጋዊ ማህተማቸውን በማሳረፍና የዋጋ ማቅረቢያውን ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ 1 ክልል ርዕሰ መስተዳድርና ካብኔ ጉዳዮች ጽ/ቤት በማለት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ለግልጽ ጨረታው የተዘጋጀውን ዝርዝር መግለጫ /መመሪያ በደንብ ማንበብ ዋጋ ሲሞላ ከሚደርሰው ስህተት ያድናል፡፡
  3. የዋጋ ማቅረቢያ ሲሞላ ስህተት ቢደረግ የግልጽ ጨረታ ሳጥኑ ከመታሸጉ በፊት ስህተቶቹን በጽሑፍ በማረምና በሌላ ፖስታ በማድረግ ፖስታው ላይ የተሻሻለ ወይም የተለወጠ የሚል ጽሑፍ ጽፎ በግልጽ ጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት ይቻላል፡፡
  4. ማንኛውም ተጫራች ሌሎች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም አቅርቦ ቢገኝ ከውድድሩ ውጪ ይደረጋል፡፡
  5. የግልጽ ጨረታ ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያቸው ላይ የሚሰጡት በግልጽ ጨረታው የሚያቀርቡትን የተወዳደሩበትን ዕቃ ዓይነት ፣ መለኪያ እና ያንዱን ዋጋ መሆኑን ካረጋገጡ በኋላ መሆን ይገባዋል፡፡
  6. የዋጋ ማቅረቢያ ሲሞላ ስርዝ ድልዝ እንዲኖረው አይፈቀድም ፣ በእርሳስ እና በቀይ እስክርቢቶ የተሞላ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራቾች ግልጽ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ያቀረበውን ዋጋ መለወጥ ፣ ማሻሻል ወይም ውድድሩን ትቻለሁ ቢል ለግልጽ ጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ገንዘብ ይቀጣል እንደ አስፈላጊነቱም መ/ቤቱ ወደ ፊት በሚያወጣው ግልጽ ጨረታ ላይ እንዳይሳተፍ ሊደረግ ይችላል፡፡
  8. ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አሸናፊ የሆኑባቸውን የዕቃ አቅርቦት ዋጋ በግልጽ ጨረታ ሰነዶች ላይ ባቀረቡት ዋጋ ብቻ ለመ/ቤታችን ማቅረብ አለባቸው ::
  9. ተጫራቾች በዝርዝር በተገለጹት የዕቃ ዓይነቶች ባላቸው የፈቃድ አይነት የሽያጭ ዋጋ በሙሉም ሆነ በከፊል መወዳደር ይጠበቅባቸዋል፡፡
  10. ተጫራቾች የግልጽ ጨረታውን ዋጋ ፀንቶ በሚቆይበት ጊዜ በግልጽ መረዳትና በተግባር ላይ ማዋል አለባቸው፡፡
  11. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ዕቃዎች ሽያጭ የዋጋ ሁኔታ መ/ቤቱ በጠየቀው ስፔስፊኬሽን መሠረት መሆን አለበት::
  12. ተጫራቾች ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣ የዘመኑ ግብር የተከፈለበትን የቫት ተመዝጋቢና የምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒውን ከዋናው ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
  13. ግልጽ ጨረታው በአየር ላይ ከሚቆይበት ቀናት ውጪ ዘግይተው የሚቀርቡ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
  14. ግልጽ ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ከ15 ተከታታይ ቀናት ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ክፍት ሆኖ ይቆይና በመጨረሻው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጨረታው ተዘግቶ በማስታወቂያ ከወጣበት በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡10 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  15. ግልጽ ጨረታው በተጫራቾች ፊት በግልጽ ይነበባል ፣ የግልጽ ጨረታ አከፋፈት ዝርዝር ቃለ ጉባዔ ተይዞ በመ/ቤቱ ጨረታ ኮሚቴ ይፈረማል እንዲሁም በግልጽ ጨረታው አከፋፈቱ ላይ የተገኙ ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በግልጽ ጨረታው አከፋፈት ስነ-ስርዓት ላይ ስለመገኘታቸው እንዲፈራረሙ ይደረጋል፡፡
  16. የአገልግሎት ጊዜው መ/ቤቱ የግልጽ ጨረታውን አሸናፊ ከለየ በኃላ አሸናፊውን ድርጅት በጽሁፍ ያሳውቃል፡፡
  17. መ/ቤቱ የግልጽ ጨረታ አሸናፊውን ለይቶ ካሳወቀ በኋላ በ3 ቀናት ውስጥ በቀረበው ዋጋ መሰረት ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ውል ይገባል፡፡
  18. የግልጽ ጨረታን በሚመለከት ጨረታውን ለማሸነፍ እንዲረዳው ለማንኛውም ኃላፊ እና ሠራተኛ መደለያ የሰጠ ተጫራች ከግልጽ ጨረታው የሚሰረዝ እና አሸንፎም ውል ቢዋዋል ውሉ የሚሰረዝ መሆኑንና በህግ የሚያስቀጣው እንደሆነ ማወቅ ይኖርበታል፡፡
  19. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት ለእያንዳንዱ ሎት ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) 10,000 /አስር ሺህ/ ማስያዝ ይኖርበታል ቢድ ቦንድ ማስያዝ ፈጽሞ አይፈቀድም፡፡
  20. በዚህ የግልጽ ተጫራቾች መመሪያ ላይ የተገለጹትን ያልፈጸመ በተራ ቁጥር 19 ላይ የተመለከተውን የጨረታ ማስከበሪያውን ሊያስቀጣው ይችላል፡፡
  21. ተጫራቾች በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ /ፖስታ/ በማሸግ ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ቤ/ጉ/ ክልል አሶሳ ከተማ በሚገኘው በጽ/ቤቱ ግዢና ንብረት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 104 በመቅረብ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  22. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ግልጽ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
  23. ሁሉም ተጫራቾች ግልጽ ጨረታው ከሚከፈትበት ቀን በፊት ሙሉ በሙሉ የግልጽ ጨረታ ሰነዳቸውን ቀድመው ካስገቡ የጨረታ መክፈቻ ጊዜውን ሳይጠብቅ ለተጫራቾች ጥሪ ተደርጎ ይከፈታል፡፡
  24. ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ አሶሳ ከተማ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና ካብኔ ጉዳዮች ጽ/ቤት ግዢና ንብረት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 104 ይከፈታል፡፡

ስልክ ቁጥር ፡- 09 21-17-78-90 ፤ 057-775-24-99 ፤ 057-775-0142፤ 057-775-00-31 ፤ 09 15-89-09-36

 

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር ም/ቤት

 

Save Tender