በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር የቢሾፍቱ ከተማ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ድርጅት በ2017 ለሥራ የሚገለገልበትን Lot 1 የ(TVS) ባጃጅ የተለያዩ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የቢሾፍቱ ከተማ የመጠጥ ውሃ ትነት አገልግሎት ድርጅት
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር የቢሾፍቱ ከተማ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ድርጅት በ2017 ለሥራ የሚገለገልበትን ፡-
Lot 1 የ(TVS) ባጃጅ የተለያዩ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
- ህጋዊ እና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (VAT) ያላቸው፤
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚንስቴር ወይም በሌላም በሚመለከታቸው ፈቃድ ሰጪ አካላት አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው ተጫራቾች ብቻ መካፈል ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አምስት (15) ተከታታይ ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በመ/ቤቱ ቀርቦ መግዛት ይቻላል፡፡
- ለጨረታ ማስከበሪያ ጠቅላላ ካቀረቡት የዕቃ ዋጋ ብር 1% በተረጋገጠ ባንክ (CPO) በድርጅቱ ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የእቃውን ስፔስፊኬሽን ከድርጅቱ በቀረበው መሠረት በግልፅ በመፃፍና ዕቃው ላይ በግልፅ መታየት ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለፁትን ማንኛውም ሁኔታዎች መለውጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይችልም፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሲያቀርቡ ቫት ያጠቃለለና ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎችን አሟልተው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የቢሾፍቱ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ቀርቦ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በ15 ቀን አስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ተከታታይ ቀናት ጠብቆ በ15ኛ ቀን እስከ ቀኑ በ8፡00 ሰዓት ጨረታው ተዘግቶ በዛው ቀን በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡ ፡ በእለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል ጽፈው መፈረም አለባቸው።
- ድርጅቱ ከሰጠው ስፔስፊኬሽን ውጪ ማስተካከያ ማድረግ እና መሰረዝ (Material Devotion) አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች በድርጅቱ ዋጋ ማቅረቢያ የድርጅቱ ኦሪጅናል ማህተም (የቢሾፍቱ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት የሚል ማህተም) ባረፈበት ላይ ብቻ የዕቃው ዋጋዎችን ሞልቶ ማቅረብ አለባቸው፤ ከድርጅቱ ዋጋ ማቅረቢያ ውጪ የሚመጡ ሰነዶች ዋጋ የላቸውም፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በድርጅታችን ግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክተር በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-4-37-16-83 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ።
የቢሾፍቱ ከተማ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ድርጅት
