Tender Detail

Tender Details

  • Deadline22 Jan 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Construction Vehicle

በአብክመ ኦሮ/ብሄ/ዞን በደዋ ጨፋ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በወረዳው ስር ለሚገኘው የሸክላ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት በከተማው የውስጥ ለውስጥ የጠጠር መንገድ በ2017 በበጀት ዓመት 10.561 ኪ.ሜ የሚሆን በከተማው የውስጥ ለውስጥ የጠጠር መንገድ ስራ ለማሰራት በቅርብ ጊዜ የተመረቱ የተለያዩ ማሽነሪዎችን ማለትም (ገልባጭ መኪና 16 ሜትር ክዩብ መጫን የሚችል፣ ሎደር፣ ኤክስካቫተር፣ ግሬደር፣ ሮሎና ሻወር ትራክ) በሰዓትና በቢያጆ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ  ቁጥር /2017 ዓ.ም

 

በአብክመ ኦሮ/ብሄ/ዞን በደዋ ጨፋ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በወረዳው ስር ለሚገኘው የሸክላ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት በከተማው የውስጥ ለውስጥ የጠጠር መንገድ በ2017 በበጀት ዓመት 10.561 ኪ.ሜ የሚሆን በከተማው የውስጥ ለውስጥ የጠጠር መንገድ ስራ ለማሰራት በቅርብ ጊዜ የተመረቱ የተለያዩ ማሽነሪዎችን ማለትም (ገልባጭ መኪና 16 ሜትር ክዩብ መጫን የሚችል፣ ሎደር፣ ኤክስካቫተር፣ ግሬደር፣ ሮሎና ሻወር ትራክ) በሰዓትና በቢያጆ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን፡፡

መስፈርቶቹም ፡-

  • ማሽነሪዎቹ በስራ ላይ እያሉ የሚጠቀሙት ነዳጅና ቅባት እንዲሁም ለሚያጋጥም ብልሽት የባለንብረቱ ሃላፊነት ሲሆን ብልሽቱ ሌሎች ማሽነሪዎች ላይ የስራ መጉላላት ሊያስከትል ስለሚችል ፈጥኖ ማስተካከል ወይም መቀየር ይኖርባቸዋል፡፡
  • የግንባታው ጠጠር የሚጓጓዘው በ 2 ኪሎ ሜትር ራዲየስ ውስጥ ነው፡፡
  1. በዘመኑን የንግድ ፈቃድ፤ የቫት ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፤ የምስክር ወረቀት እና እንዲሁም አንድ ዓመት ያልሞላው ወይም የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. በዘርፉ በ2017 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤
  3. የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው የሚያሳይ ማስረጃ አብረው ማቅረብ የሚችሉ፤
  4. ተጫራቾች የምዝገባ የምስክር ወረቀት/ቲን ነምበር አብረው ማያያዝ ይኖርባቸዋል፤
  5. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ 1 ፐርሰንት እና ከዚያ በላይ ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይንም በገቢ መቀበያ ደረሰኝ በአብክመ ኦሮ ብሄ/ን በደዋ ጨፋ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በወረዳው ስር ለሚገኘው የሸክላ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት ስም በምርጫቸው በአንዱ ከዋና /Original/ የመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የሚያሳይ የጨረታ ሰነድና የተጫራቾች መመሪያ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከ22/4/2017 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እሰከ 21ኛው ቀን ማለትም እስከ 13/5/2017 ዓ.ም ማከሰኞ ቀን 11፡30 ሰዓት ድረስ በአብከመ ኦሮ/ብሄ/ዞን በደዋ ጨፋ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በወረዳው ስር ለሚገኘው የሸክላ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት ለመንገድ ስራ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን ዋና እና ቅጂ /Original and Copy/ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ከ22/4/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 22ኛው ቀን ማለትም እስከ 14/5/2017 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በአብክመ ኦሮ/ብሄ/ዞን በደዋ ጨፋ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በወረዳው ስር ለሚገኘው የሸከላ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ22ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ4:30 ሰዓት በግልጽ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ዕለቱ የበዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡
  9. የጨረታው ውጤት ለአሸናፊ ድርጅቶች በአድራሻ ለተሸናፊዎች ደግሞ በግልባጭ በደብዳቤና በማዘጋጃ ቤቱ የውስጥ ማስታወቂያ የምናሳውቅ ይሆናል፡፡
  10. ተጫራቾች በሌላ ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተመስርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
  11. ማዘጋጃ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ ፡- ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ መስመር 332 KM ላይ በአብክመ ኦሮ/ብሄ/ዞን በደዋ ጨፋ ወረዳ ሸክላ ከተማ እንገኛለን፡፡

ስልክ ቁጥር ፡- 09-10-24-55-51/ 09-21-03-00-49 ላይ በመደወል ማንኛውንም መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

በአብክመ ኦሮ/ብሄ/ዞን በደዋ ጨፋ ወረዳ የሸክላ ከተማ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት

 

Save Tender