ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለጹትን እቃ/አገልግሎት ግዥ ለመፈጸም ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
SPA SERVICE ENTERPRISE (የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት)
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የእቃ/ አገልግሎት ግዥ
ጨረታ ማስታወቂያ
ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለጹትን እቃ/አገልግሎት ግዥ ለመፈጸም ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በዚህ
መሠረት ፡-
ሎት 1 - የቅቤ አቅርቦት ግዥ፣
ሎት 2 - የአትክልት አቅርቦት ግዥ፣
ሎት 3 - ተቆልቶ የተፈጨ ቡና ግዥ፣
ሎት 4 - የአሣ አቅርቦት ግዥ ሲሆኑ
ተጫራቾች የሚከተሉትን መመሪያዎች በማሟላት ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው።
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ሕጋዊና የታደሰ የ2017 ዓ.ም ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ TIN እና VAT ሰርተፊኬት ያላቸው፣ የገቢዎች ክሊራንስና ጨረታ ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢ የተሰጣቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የገቢዎች ክሊራንስና ጨረታ ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢ የተሰጣቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ከገንዘብና ኢካኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢዎች ዝርዝር የምዝገባ ፈቃድ የተመዘገቡና የቅርብ ጊዜ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ለእያንዳንዱ የጨረታ ማስከበሪያ 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ብቻ ማስያዝ አለባቸው።
- ለጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በድርጅታችን አዲሱ ፍልውሃ ሆቴል እንግዳ መቀበያ በመክፈል ከድርጅቱ ግዥ አቅርቦት ቡድን መሪ ቀርበው የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊትና ከነቫቱ ተብሎ በኢትዮጵያ ብር መገለጽና መሆን አለበት። ተጫራቾች በጨረታው ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፤ ሙሉ አድራሻቸውን፣ ፊርማቸውን እና ማህተም አሟልተው ማቅረብ አለባቸው::
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተሰጠ ዋጋን መለወጥ አይቻልም። እቃው የሚቀርብበት ጊዜ ቦታና ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ መገለጽ አለበት። ስለ እቃው ዋስትናና የዋስትና ጊዜ በግልጽ መገለጽ አለበት።
- ጨረታውን በሚመለከት ለማሸነፍ እንዲረዳዎት ለማንኛውም ኃላፊና ሰራተኛ መደለያ የሰጠ ተጫራች ከጨረታ የሚሰረዝ ሲሆን አሸንፎም ውል ቢዋዋል ውሉ ይሰረዛል።
- ድርጅታችን የዋጋ ለውጥ ሳይኖር በመጠን ወይም በዋጋ እስከ 25% በመጨመር ወይም 20% ቀንሶ መግዛት እንደሚችል በቅድሚያ መታወቅ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከቫት በፊት ወይም ከቫት ጋር በግልጽ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥር 9 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው በእለቱ በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል።
- ተጫራቾች በሚጫረቱበት የግዥ አይነት መሠረት የተሟላ የቴክኒካል ሰነድ እና ፋይናሽያል በተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ /Bid document/ መሠረት የጨረታ ሰነዳችሁ ማስገባት ይኖርባችኋል። የጨረታው ቴክኒካል ፕሮፖዛል ሰነድ ለብቻው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ /CPO/ ለብቻው እና ፋይናሽያል ሰነድ ለብቻው በጨረታ ሣጥኑ ማስገባት አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሂደቱ የቴክኒክ ግምገማ ድርጅቱ በሚያወጣው መስፈርት መሠረት ቴከኒካል ሰነድ ግምገማ፣ ድርጅታዊ ብቃት ግምገማ እና ናሙና ጥራት ግምገማ ውጤት (60%) እና ፋይናንሻል (ዋጋ) ግምገማ ውጤት (40%) ሲሆን ድምር ውጤት ከ100% አሸናፊ የሚለይ መሆኑን ማወቅ አለባችሁ፡፡ ነገር ግን ቴከኒካል ናሙና ግምገማ ሰነድ ወይም ድርጅታዊ ብቃት ያላለፈ ተጫራች ድርጅት ፋይናንሽያል ሰነድ እንደማይከፈት እንዲታወቅ፡፡ የመገምገሚያ መስፈርቶቹ በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ማየት ይቻላል።
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉ ሆነ በከፊል የመረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር ፡- 011-5-53-07-67/ 011-5-15-73-37
ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት
