Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅ/ፅ/ቤት
  • Address በሀዋሳ ከተማ ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ አጠገብ ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046-220-42-24
  • Website
  • Deadline14 Jan 2025, 9:30 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Labour Outsourcing Services

የኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት የጽዳት አገልግሎት በሶስተኛ ወገን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

የኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅ/ፅ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት የጽዳት አገልግሎት በሶስተኛ ወገን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቲ.ኦ.ቲ ተመዝጋቢ የሆኑ እንዲሁም የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ ሆኖ እነኝህን ማስረጃዎችን አደራጅተው ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

  • ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) እና የተጫራቾች መመሪያ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000013485236 በማስገባት አራተኛ ፎቅ የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 46 በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በCPO ብር 10,000.00 በባንክ የተረጋገጠ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው::
  • ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣ ለ15 ቀን ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ በዕለቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት አራተኛ ፎቅ የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ይከፈታል፡፡
  • ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋ ዋናውንና አንድ ኮፒ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት ድረስ በሰም የታሸገ ፖስታ በማድረግ አራተኛ ፎቅ የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
  • የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን እሁድ ወይም የበዓል ቀን ላይ የሚውል ከሆነ በቀጣዩ ቀን ይከፈታል።
  • ቢሮው ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማብራሪያ ቢያስፈልግዎ በስልክ ቁጥር 046-220-42-24/046-212-34-68 ይጠቀሙ።

አድራሻ ፡- ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ አጠገብ፡፡

 

የኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት

 

Save Tender