የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ በ2017 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ አላቂ የጽሕፈት መሳሪያዎችን፣ ተሽከርካሪ ሞተር ሳይክል እና ቋሚ የቢሮ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ በ2017 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ አላቂ የጽሕፈት መሳሪያዎችን፣ ተሽከርካሪ ሞተር ሳይክል እና ቋሚ የቢሮ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- በግብር ከፋይነት ተመዘግበው የአቅራቢነት ሠርተፊኬት ኖሯቸው የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝገቢ ሆነው የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ እንዲሁም በጨረታ መሳተፍ የሚችሉበትን የጊዜ ገደብ የሚገልፅ ከሚመለከተው አካል የተሰጠ ማስረጃ በመያዝ የማይመለስ ብር 100.00 በመከፈል ሰነድ በመግዛት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ ግዥ ፋይናንስ ንብ/አስ/ዳይ/ ቢሮ ቁጥር 7 በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀረቡት የጨረታ ሰነድ የውል ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በሕጋዊ ባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ በማዘጋጀት ኦሪጅናልና ኮፒ ፖስታዎችን ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከጨረታ መመሪያ ጋር አባሪ ተድርጎ ተያይዟል፡፡
- ይህ ጨረታ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በዓል ቀን ከሆነ የጨረታ መክፈቻው ዕለት በተጠቀሰው ሰዓት በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ዝርዝር ሰነድ ላይ ስምና አድራሻ በግልፅ በመሙላት በማሕተምና ፊርማ ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል:: አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች መመሪያ ባለማክበራቸው የሚፈፀም ማንኛውም ስህተት ኃላፈነቱ የተጫራቾች ይሆናል።
- ኤጀንሲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ
ሀዋሳ ወደ ሪፈራል በሚወሰደው መንገድ ሳይ ከሂል -ሳደድ ሆቴል በስተ-ጀርባ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ ግዥ ፋይናንስ
ንብ/አስ/ዳይ/ ቢሮ ቁጥር 7
ስለ ጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግዎ በዚህ ስልክ ቁጥር ይደውሉ
0926023734 ወይም 0916504169
የሲዳማ ብ/ክ/መንግስት የሙያ ብቃት ማረጋጋጫ ኤጀንሲ
