የወሎ ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት አድራሻ ደሴ ከተማ ሚገኘውን በስጦታ የተላለፉ የተለያዩ መጠን ያላቸው ያገለገሉ ጎማዎችን እና የመኪና ባትሪ በሽያጭ ኮሚቴ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የወሎ ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት
የጎማ ሽያጭ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ያገለገለ ጎማና ባትሪ በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የወሎ ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት አድራሻ ደሴ ከተማ ሚገኘውን በስጦታ የተላለፉ የተለያዩ መጠን ያላቸው ያገለገሉ ጎማዎችን እና የመኪና ባትሪ በሽያጭ ኮሚቴ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሠረት በጨረታው መሳትፍ የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች በመወዳደር መግዛት የሚችሉ መሆኑን ይገልጻል፡-
- በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያለው ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት በጨረታው መሳተፍ ይችላል፤
- ተጫራቾቹ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ምዝገባና የዘመኑ ግብር የከፈሉበት ማስረጃ ያላቸው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ዕለት ከ21/04/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 06/05/2017 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ 200 ሁለት መቶ ብር በመክፈል ጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ወሎ ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት ግዥና ፋይ/ንብ አስ/ደ/ የስራ ሂደት ደሴ ከተማ ቢሮ በመቅረብ መውሰድ 1 ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋውን 2% በሽያጭ ኮሚቴ በከፈተው አካውንት ቁጥር ገቢ በማድረግ ዲፖዚት ስሊፕን ዋጋ በተሞላበት ፖስታ በማሸግ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የተለያዩ መጠን ያላቸው ያገለገሉ ጐማ እና የመኪና ባትሪ በጨረታ ሰነዱ ላይ ባለው ዝርዝር መሰረት ተጫራቾች በሙሉ መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ያገለገሉ ጎማዎች እና የመኪና ባትሪ የዋጋ ውድድሩ የሚካሄደው ወይም አሸናፊ የሚለው በሎት (በጥቅል) ዋጋ ድምር ይሆናል፡
- አሸናፊ ተጫራች ከታወት በኋላ ለመልካም የስራ አፈጻጸም ዋስትና የጠቅላላ ዋጋ ውን 10 ፐርሰንት የተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ ለመ/ቤቱ ማድረግ ይጠበቅበታል።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ግልጽ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት 15 ቀናት ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በታሸገ ፖስታ ወሎ ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት ደሴ ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 6/5/2017 ዓ.ም ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- ኮሚቴው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ የሚመረቱትን የተለያዩ መጠን ያላቸው አሮጌ ጎማዎች እና የመኪና ባትሪ ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ውድድር የሚደረገው ወይም አሸናፊ የሚለየው በሎት በጠቅላላ ከፍተኛ ዋጋ የሞላ ብቻ ይሆናል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባልተገኙበት ኮሚቴው በ6/5/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ተዘግቶ በ ሰዓት ይከፈታል፡፡ እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0331116229 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
የወሎ ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት
