የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ቢሮ ለ2017 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት እና በስሩ ለሚገኙ አዲስ ለተከፈቱ የቴ/ሙ/ት/ስ/ኮሌጆች ለስልጠና አገልግሎት የሚሆኑ የተለያዩ የጽህፈት መሣሪያዎች፤ የጽዳት ዕቃዎችን ፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ሞተር ሣይክል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ቢሮ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር - 01/2017
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ቢሮ ለ2017 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት እና በስሩ ለሚገኙ አዲስ ለተከፈቱ የቴ/ሙ/ት/ስ/ኮሌጆች ለስልጠና አገልግሎት የሚሆኑ የተለያዩ የጽህፈት መሣሪያዎች፤ የጽዳት ዕቃዎችን ፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ሞተር ሣይክል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት ፡-
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፣ በግብር ከፋይነት ተመዝግቦ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለውና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፣ የ2016 ዓ.ም የግብር ግዴታውን የተወጣ፣ ከሚመለከተው አካል የሚሰጥ የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው እንዲሁም በጨረታ ለመሳተፍ የሚችልበት የጊዜ ገደብ የሚገልጽ ከሚመለከተው አካል የተሰጠ ማስረጃ በመያዝና ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በአርባ ምንጭ በሚገኘው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ቴክኒከና ሙያ ትምህርት ስልጠና ቢሮ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ::
- ማንኛውም ተጫራች ከሚያቀርቡት የጨረታ ሠነድ ጋር የጨረታ ማስከበሪያ ለጽህፈት መሣሪያ ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/፣ ለጽዳት ዕቃዎች ብር 3,000.00 /ሶስት ሺህ ብር/፣ ለኤሌክትሮኒክስ ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ እና ለሞተር ሣይክል 15,000.00 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ CPO በማዘጋጀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ::
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ዝርዝር ሰነድ ላይ ስምና አድራሻቸውን በግልጽ በመሙላት በማህተምና ፊርማ ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል። የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ የሌለው ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ዝርዝር ስርዝ ድልዝ የሌለው በግልጽ የሚነበብ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ኦሪጅናልና ኮፒ ፖስታዎችን ለየብቻ በማሸግ በአንድ እናት ፖስታ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል እንዲሁም ለኤሌክትሮኒክስ እና የሞተር ሣይክል የቴክኒካልና ፋይናንሻል ኦሪጅናልና ኮፒ ፖስታዎችን ለየብቻ በማሸግ በአንድ እናት ፖስታ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ በታወጀ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡ 30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። (16ኛው ቀን በሥራ ቀን ካልዋለ በቀጣዩ የስራ ቀን ይሆናል)።
- ጨረታው ዋጋ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0461814358 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ቴክኒክና ሙያ
ትምህርት ሥልጠና ቢሮ
አርባ ምንጭ
