Tender Detail

Tender Details

  • Company በማ/ኢ/ክ/መ/ ምስራቅ ጉራጌ ዞን የሶዶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ : በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0468 83 05 33
  • Website
  • Deadline13 Jan 2025, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Vehicle Battery

በምስራቅ ጉራጌ ዞን የሶዶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ሎት 1 የተሽከርካሪ መኪና ጎማና መለዋወጫ፣ ሎት2 የተሽከርካሪ ሞተር ብስክሌት ጎማና መለዋወጫ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በማ/ኢ/ክ/መ/ ምስራቅ ጉራጌ ዞን የሶዶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር 04/2016

 

በምስራቅ ጉራጌ ዞን የሶዶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ሎት 1 የተሽከርካሪ መኪና ጎማና መለዋወጫ፣ ሎት2 የተሽከርካሪ ሞተር ብስክሌት ጎማና መለዋወጫ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

  1. የዘመኑ ግብር የከፈሉ እና ስለመክፈላቸው ከገቢዎች ጽ/ቤት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
  2. ቲን ነምበር ያላቸው እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤
  3. የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፤
  4. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
  5. ጨረታው የሚቆየው ከ20/4/2017 ዓ.ም እስከ 05/05/2017 ዓ.ም ሲሆን ተጫራቾች ዋጋቸውን በሁለት ፖስታ ፋይናንሻልና ቴክኒካል ለየብቻ በመሙላት ሶ/ወ/ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁ/ር 4 በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. ጨረታው የሚከፈትበት በ05/05/2017 ዓ.ም ሎት 1 በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል፣ ሎት 2 በ8፡30 ሰዓት ታሽጎ በ9፡00 ሰዓት ሶ/ወ/ፋይናንስ ጽ/ቤት የግ/ከ/ን አስ/ሥ/ሂደት ቢሮ ቁ/ር 4 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል።
  7. መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ CPO ከሎት 1 - ሎት 2 ለእያንዳንዳቸው ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  9. የጨረታ ማስከበሪያው ለተሸናፊ ድርጅት አሸናፊው ውል መግባቱ ከተረጋገጠ በኋላ ይመለስለታል።
  10. አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱን ከተረጋገጠ እስከ ሶዶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በመቅረብ ውል መፈጸም ይኖርበታል።
  11. አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች በፈረሙት ውል መሰረት አሸናፊ የሆኑባቸው እቃዎች /አገልግሎቶች/ በራሳቸው ትራንስፖርት ፋይናንስ ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ አለባቸው።
  12. ተጫራቾች የዕቃ ዝርዝር የያዘ ሰነድ ሶዶ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 በመቅረብ ከሎት 1-2 ለእያንዳንዱ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።

 

ለበለጠ መረጃ፡- 046-8-83-05-33/128

 

በማ/ኢ/ክ/መ/ ምስራቅ ጉራጌ ዞን የሶዶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender