የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን አሶሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በጉምሩከ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 61 እና 62 በተሰጠው ሥልጣን መሰረት በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ ተይዘው የተወረሱ የእርሻ ትራክተር እና ሞተር ሳይክል በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
የጉምሩክ ኮሚሽን አሶሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
ለሁለተኛ ዙር የወጣ የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር (03/2017)
የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን አሶሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በጉምሩከ አዋጅ ቁጥር 859/2006 አንቀጽ 61 እና 62 በተሰጠው ሥልጣን መሰረት በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ ተይዘው የተወረሱ የእርሻ ትራክተር እና ሞተር ሳይክል በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
- በጨረታው ላይ ለመሳተፍ ማንኛውም የድርጅት ተወካይ ወይም ግለሰብ ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ ጨረታውን መካፈል/መሳተፍ ይችላል፡፡
- ለሐራጅ ጨረታ ለትራክተር 50,000 ብር ለሞተር ሳይክል 4000 ብር ለጨረታ ዋስትና (CPO) በጉምሩክ ኮሚሽን አሶሳ ቅ/ጽ/ቤት ስም በባንከ በተረጋገጠ አሠርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ከ18/4/2017 እስከ 23/4/2017 ድረስ አሶሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በመምጣት ተሽከርካሪዎቹን ማየት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን በዚያው ዕለት ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ጨረታው የሚጀመር ይሆናል።
- ተጫራቾች ጨረታው ከመጀመሩ በፊት አስቀድመው መመዝገብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው ማካሄጃ ቦታ ጉምሩክ ኮሚሽን አሶሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ ነው፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን አሸናፊ ላልሆኑት ተጫራቾች ደግሞ በ3 የሥራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
- አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋጋ ክፍያ ከፈፀሙ በ5 ቀናት ውስጥ ተሽከርካሪዎቹን ተረክበው ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡
- ከላይ በተራ ቁጥር 7 እና 8 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ተሽከርካሪዎቹን ተረከበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለኮሚሽኑ ገቢ ሆኖ ተሽከርካሪዎቹ በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባሉ፡፡
- ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ 057-44-83-714 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽን አሶሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
