የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን በተለያዩ የመንገድ ጥገና ፕሮጀክቶች ላይ ጠጠር የሚያመላልሱ ገልባጭ መኪኖች እስከነ ሎደሩ አቅራቢዎችን ከዚህ በታች በተገለጸው መሠረት መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።
የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን (Sidama Roads Authority)
ለሶስተኛ ዙር የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዢ መለያ ቁጥር - ሲ/መ/ባ/009/2017
የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን በተለያዩ የመንገድ ጥገና ፕሮጀክቶች ላይ ጠጠር የሚያመላልሱ ገልባጭ መኪኖች እስከነ ሎደሩ አቅራቢዎችን ከዚህ በታች በተገለጸው መሠረት መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የፕሮጀክቱ ስም |
በክልል ውስጥ መንገዱ የሚገኝበት ወረዳ |
የመንገዱ ርዝመት በኪ/ሜ |
|
1 |
አለታ ወንዶ ሀዋጃ ባርጎ ሜጫ |
አለታ ወንዶ – ቡርሳ |
10 |
|
2 |
አባያ-ወታራ ጋንዶ |
ወንዶ ገነት |
6 |
በዚሁ መሠረት :-
- የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች የማከራየት ፍቃድ ያላቸው ወይም በጠቅላላ ሥራ ተቋራጭነት ከደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ ፍቃድ ያላቸው ሆነው የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ።
- ገልባጭ መኪና እስከነ ሎደር የስሪት ዘመን እ.ኤ.አ 2012 እና ከዚያ በላይ ሆኖ፣ የተሽከርካሪ የመጫን አቅም 14m3 የሆነ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች አግባብነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፊኬት፤ የግብር ከፋይነት ሰርተፊኬት እና በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም ከመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚያሳይ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- አዲስ ስራ ፈቃድ የሚያቀርቡ ተጫራቾች አንድ ፕሮጀክት ብቻ እንዲሁም ሥራ ልምድ ያላቸው ተጫራቾች ደግሞ እስከ ሁለት ፕሮጀከቶች ብቻ መወዳደር ይችላሉ።
- ከሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን ጋር ውለታ ገብቶ በአፈጻጸም ችግር ምክንያት ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት ስራውን ያላጠናቀቀና ውሉ የተቋረጠበት የገልባጭ መኪና አከራይ ድርጅት የጨረታ ሰነዱን መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችልም።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አሰራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ከባለሥልጣኑ መ/ቤት ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬከቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና (Unconditional Bid Bond) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 1% ማስያዝ ያለባቸው ሲሆን ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከላይ በተገለጸው መሠረት ይሆናል። ከባንክ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) A180 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል።
- የጨረታ ሰነዱ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ /Bid Security/ ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦሪጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (ኦሪጅናል) እና ሁለት ኮፒ ሰነዶች በተለያየ ፖስታ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ ተካተውና በሁሉም ዶከመንት ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬከቶሬት ክፍል ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ሠነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት። ሆኖም የተጠቀሰው ቀን የእረፍት ወይም የህዝብ በዓል ቀን ሆኖ ከዋለ በቀጣይ በስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ በባለስልጣኑ መ/ቤት አደራሽ ይከፈታል።
ማሳሰቢያ ፡- ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልከ ቁጥር ፡- 046-2-12-84-46
የሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን
