ድርጅታችን የአማራ መንገድ ስራዎች ድርጅት ዉል ወስዶ ለሚገነባው ለዋርካው ምድረ ገነት ዘንዘልማ አስፓልት መንገድ ስራ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል 60/70 ቤትመን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Amhara Road Works Enterprises (ARWE) (የአማራ መንገድ ስራዎች ድርጅት)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አመስድ 10/2017
ድርጅታችን የአማራ መንገድ ስራዎች ድርጅት ዉል ወስዶ ለሚገነባው ለዋርካው ምድረ ገነት ዘንዘልማ አስፓልት መንገድ ስራ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል 60/70 ቤትመን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የእቃው አይነት |
ብዛት |
ምርመራ |
|
1 |
60/70 ቢትመን |
546,000 |
|
ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለፁትን የጨረታ መወዳደሪያ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ማንኛዉም አቅራቢ ድርጅት በጨረታው መወዳደር ይችላል።
- በዘርፍ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የተ.እ.ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸዉ፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው እና የግብር ግዴታቸውን ስለመወጣታቸዉ የሚገልፅ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል በድርጅታችን ስም አማራ መንገድ ስራዎች ድርጅት (AMHARA ROAD WORKS ENTERPRISE) በሚል ጨረታው ከሚከፈትበት ቀን ጀምሮ ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲፒአ ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ የሚከፈል ባንክ ጋራንቲ ብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) ማስያዝ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ አሸናፊውን ተጫራች ድርጅት በሚመርጥበት ጊዜ የሚገዛውን እቃ መጠን እንደአስፈላጊነቱ እስከ 50% ሊቀንስ ወይም ሊጨምር ይችላል፡፡
- ተወዳዳሪ ድርጅቶች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ፋይናንሻል ሰነድ ቅጅ (ኮፒ) እና ዋና (ኦርጅናል) ለየብቻ በፖስታ በማዘጋጀት እንዲሁም የጨረታ ማሰከበሪያውን በአንድ ፖስታ ለብቻ በማድረግ በአንድ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ባህር ዳር ከተማ ከሚገኘው ዋና መ/ቤታችን አማራ መንገድ ስራዎች ድርጅት ከአማራ ፓይፕ ፋብሪካ ፊት ለፊት ግዥ ክፍል በመቅረብ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በ20ኛው ቀን 9፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 9፡30 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የመክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከአማራ መንገድ ስራዎች ድርጅት ፋይናንስ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 23 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058-320-35-76 መደወል ይችላሉ፡፡
የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት
