Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ጥበቃ ቢሮ የሸዋሮቢት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
  • Address በደሴ መስመር በሚወስደው አስፋልት ከሸዋ ሮቢት ከተማ 3 ኪሎ ሜትር አለፍ ብሎ ወደ ምዕራብ 500 ሜትር ገባ ብሎ : አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 09 20 20 56 42
  • Website
  • Deadline08 Jan 2025, 9:30 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Electronics Materials

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ጥበቃ ቢሮ የሸዋ ሮቢት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ግብአቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ጥበቃ ቢሮ የሸዋሮቢት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ  ቁጥር 03/2017

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ጥበቃ ቢሮ የሸዋ ሮቢት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ግብአቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት 1. የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎች

ሎት 2. የተለያዩ የፅዳት ግብአቶች

ሎት 3. የተለያዩ ህትመቶች

ሎት 4. የኤሌትሮኒክስ እቃዎች

ሎት 5. የውሃ ቧንቧ መገጣጠሚያ እቃዎች

በዚህም መሰረት፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN / ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ከብር 200,000 በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  4. ውድድሩ የሚሰላው በጥቅል ዋጋ ስለሆነ ለተዘረዘሩት እቃዎች ለሁሉም ዋጋ መስጠት አለበት፡፡
  5. የጨረታ ሰነዱን በብር 300 /ሶስት መቶ/ በመክፈል ከሆስፒታሉ ግ/ፋይ/ንብ/አስ/ደ/የስ/ ሂደት ቢሮ መውሰድ ይቻላል፡፡
  6. የጨረታ ማስከበሪያ ያስገቡትን ጠቅላላ ዋጋ 1% ያከሉን ለሆስፒታሉ በCPO /በመሂ1 ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  7. ከብር 3000 /ሶስት ሺህ/ በላይ ለአገልግሎት ግዥ እና ከብር 10,000 /አስር ሺህ/ በላይ ለሚገዙ ግዥዎች 2% የመቁረጥ እና በስማቸው የታተመ ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  8. ለሁሉም ሎቶች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ሙሉ አድራሻቸውን ስማቸውን ፊርማቸውን እና የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
  9. አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 የሥራ ቀናት ውስጥ ውል ማስከበሪያ 10% ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ በCPO በማስያዝ ውል መውሰድ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  10. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ዝርዝር አባሪ ዶክመንቶችን ጨምሮ የጨረታ ሰነዱን ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በፖስታ አሽገው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ጨረታው ክፍት ሆኖ የሚቆየው ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን ጠዋት 3፡30 ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን 4፡00 ላይ ይከፈታል፡፡
  12. ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ እና ሰዓት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በሆስፒታሉ በመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቻው የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት አያግድም፡፡
  13. ለሁሉም ሎቶች ተጨማሪ መረጃዎችን ከጨረታው መመሪያና ከዋጋው መሙሊያ ላይ ማግኘት ይቻላል።
  14. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የመንግስት የሥራ ቀን ካልሆነ /ዝግ ከሆነ በቀጣዩ ባለው የሥራ ቀናት ይከፈታል፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09 20 20 56 42 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

አድራሻ ፡- በደሴ መስመር በሚወስደው አስፋልት ከሸዋ ሮቢት ከተማ 3 ኪሎ ሜትር አለፍ ብሎ ወደ ምዕራብ 500 ሜትር ገባ ብሎ እንገኛለን፡፡

 

በሰሜን  ሸዋ  ዞን  የሸዋ  ሮቢት  የመጀመሪያ  ደረጃ  ሆስፒታል

 

Save Tender