Tender Detail

Tender Details

  • Company የአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address አምቦ ከተማ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0112609448
  • Website
  • Deadline14 Jan 2025, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Construction Vehicle

የአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2017 የበጀት ዓመት ጋራጋንቲ የሚያመርት ዶዘር መከራየት ስለሚፈልግ መስፈርቶችን የሚያሟሉ አቅራቢ ድርጅቶችን በማወዳደር መከራየት ይፈልጋል፡፡

የአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት


ለመጀመሪያ ግዜ የወጣ ግልጽ የግዥ

ጨረታ ማስታወቂያ  የግዥ መለያ ቁጥር 02/2017

 

የአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2017 የበጀት ዓመት ጋራጋንቲ የሚያመርት ዶዘር መከራየት ስለሚፈልግ መስፈርቶችን የሚያሟሉ አቅራቢ ድርጅቶችን በማወዳደር መከራየት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ፡-

  1. ከተጠቀሰው ሥራ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያለዉ: የ 2017 የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈለ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin Number) ያለው፤ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ፤ እንዲሁም በአቅራቢዎች ዝርዝር (supplier list) የተመዘገበ ሆኖ ከሚመለከተው አካል ማስረጃውን ፎቶ ኮፒ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡ በተጨማሪም ከሚያገኘው ገቢ ላይ 2% ታክስ ለመክፈል ፍቃደኛ የሆነ፡፡
  2. ከሙስና እና መሰል ብልሹ አሠራር ድርጊቶች ነጻ የሆነ እና የሀገሪቱን እና የክልሉን ሕግ የሚያከብር፡፡
  3. ማንኛውም ተጫራቾች በአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ስም ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) የገንዘብ መጠን ህጋዊ እና እውቅና ካለው ባንክ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  4. የጨረታ አሸናፊው ካሸነፈ በኋላ ከጠቅላላ ዋጋ ላይ የጨረታ ውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
  5. በጨረታ ሠነዱ ላይ ስልጣን ባለው አካል /የድርጅቱ ባለቤት/ ሥም፤ ፊርማ፤ የድርጅቱን ማህተም፤ የድርጅቱን ሙሉ አድራሻ እና ስልክ ቁጥር በፖስታ ላይ መገለጽ አለበት፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታውን ኦርጅናል ከኮፒው ጋር በታሸገ ፖስታ አድርጎ ለየብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  7. ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ-06/05/2017 8፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚያው ዕለት በ8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
  8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአምቦ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 07 ይከፈታል፡፡ ጨረታዉ በሚከፈትበት ቀን ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባለመገኘታቸው ምክንያት ጨረታውን ከመክፈት አያስቀርም፡፡ ጨረታው የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት የአድራሻ ለውጥ ካለ በውስጥ ማስታወቂያ የምናሳውቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  9. የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺህ/ ሾርት ኮድ (short code) 518220 ኦብሬተር አይድ (Operator ID) 176959 ላይ በቴሌ ብር በማስገባት የአምቦ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን የሚሰጣቸውን ደረሰኝ በመያዝ የጨረታ ሰነዱን ከአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 07 መውሰድ ይችላሉ፡፡
  10. ጨረታውን ለማደናቀፍ የሚሞክር ከጨረታው ውጪ እንዲሆን ተደርጎ ለወደፊት በማንኛውም የመንግስት ግዥ እንዳይሳተፍ ይደረጋል፡፡
  11. አሸናፊ የሆነ ድርጅት በራሱ ወጭ እስከ ሳይት ዶዘሩን ጭኖ የሚያመጣ እና አምርቶ ሲጨርስም በራሱ ወጭ የሚወስድ መሆን አለበት፡፡
  12. በሳይት ቆይታው የዶዘሩን ጥበቃ፤ የኦፕሬተር ውሎ አበል ፤ ነዳጅ እንዲሁም ሌሎች ወጭዎችን በአሸናፊው የሚሸፈን ይሆናል፡፡
  13. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

  አድራሻ ፡- የአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

ስልክ ቁጥር ፡- 0112609448/0112364462

 

የአምቦ  ከተማ  አስተዳደር  ገንዘብ  ጽ/ቤት

Save Tender