Tender Detail

Tender Details

  • Company በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ
  • Address ሠመራ ፡ አፋር ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 033-366-60-22
  • Website
  • Deadline06 Jan 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Vehicle tire

የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት የትራክተር ኪራይና የመኪና ጎማ እና የተለያዩ የግብርና ግብዓት ግዥ ለመፈጸም በአገር ውስጥ ገበያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት የትራክተር ኪራይና የመኪና ጎማ እና የተለያዩ የግብርና ግብዓት ግዥ ለመፈጸም በአገር ውስጥ ገበያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተለገጹትን ነጥቦች ማሟላት ይኖርባቸዋል።

  1. ተጫራቾች ግዴታ ማሟላት ያለባቸው የቅድሚያ መወዳደሪያ መስፈርቶች ማለትም፤
    1. በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ
    2. የንግድ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ያለው
    3. ንግድ ፈቃድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ያለው
    4. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ
    5. ሲ.ፒ.ኦ
    6. የጨረታ ሰነዱ ግዥ የፈጸመ እና
    7. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያለው ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ።
  2. በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታውን ሰነድ ከአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ ግዥ/ፋይ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ክፍል ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች በእያንዳንዱ በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነዶች ላይ ተጫራቾች ወይም የህጋዊ ወኪል ፊርማና ማህተም ማኖር ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /Bid Bond/ ለውድድር የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 1% በሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል። የጨረታ ተወዳዳሪዎች በውድድሩ ከተሸነፉ ለዋስትና ያስያዙት የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና የጨረታው ውጤት ታውቆ ውል ከተፈራረሙ በኋላ ወዲያውኑ የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና ያስያዙት የውል ማስከበሪያ ይመለስላቸዋል።
  5. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርቡትን የውድድር ጥያቄ መ/ቤቱ አይቀበልም።
  6. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 የስራ ቀናት የሚቆይ ሆኖ በ15ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋ ሲሆን በእለቱ 4፡30 ሰዓት በአፋር ብሄራዊ ክ/መ/ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  7. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  8. ለተጨማሪ መረጃ በቢሮው ስልክ ቁጥር 033-366-60-22 ወይም 033-366-33-76 ደውለው ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

 

በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ

ሠመራ

Save Tender