የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ለ2017 በጀት ዓመት የመኪና ጎማ በጨረታ ለማውጣት ስለምንፈልግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል።
Dire Dawa Administration Police Commission (የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን)
የጨረታ ማስታወቂያ
የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ለ2017 በጀት ዓመት የመኪና ጎማ በጨረታ ለማውጣት ስለምንፈልግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል።
- የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ለ15 ተከታታይ ቀናት በድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን ፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት የሥራ ሒደት ቢሮ ቁጥር 16 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የዘመኑን የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር ከፋይ የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ ፣ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆንና የጨረታው ውጤት እንደታወቀ የሚመለስ የሚጫረቱበትን እቃ ዋጋ 2% /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- በተዘጋጀው የጨረታ ሠነድ ላይ ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ተመራጭነት አለው፡፡
- የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት ለየብቻ በፖስታ በማሸግ በአንድ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ በጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነድ 14/4/2017 ዓ.ም እስከ 28/4/2017 ዓ.ም ከ11:00 ሰዓት በድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን በፋይናንስና ግዢ አስተዳደረ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 16 ቀርበው መግባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 29/4/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ታሽጎ 3፡30 ሠዓት ይከፈታል፡፡
- ፖሊስ ኮሚሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር ፡- 0251-11-74-55/0251-11-37-43 በመደወል
መረጃ ፖ.ሣ.ቁጥር 1453 ማግኘት ይችላሉ፡፡
የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን
