በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዋዳ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ለ 2017 በጀት ዓመት በግዥ መለያ ቁጥር HU/ ABEC//11/11/55/17 የመኪና ጎማ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዋዳ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ
በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዋዳ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ለ2017 በጀት ዓመት በግዥ መለያ ቁጥር HU/ ABEC//11/11/55/17 የመኪና ጎማ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም :-
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ ከፌደራል ሃገር ውስጥ ገቢ ወይም ከሌሎች ግብር ሰብሳቢ የመንግስት መ/ቤቶች ወቅታዊ የግብር ግዴታቸውን የተወጡና በመንግስት ጨረታዎች መካፈል የሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ፤ በፌዴራል ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የመረጃ መረብ /Website/ ላይ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያሳይ ማስረጃ እና የሚጫረቱበት ዋጋ ከብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) የሚበልጥ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚቀርበው ቢድ ቦንድ ወይም ሲፒኦ የባንክ ጋራንቲ መሆን ያለበት ሲሆን 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንከ ለመኪና ጎማ የጨረታ ማስከበሪያ ሲሆን ሃምሳ ሺህ ብር (50,000.00) በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም የባንክ ጋራንቲ የጨረታው ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በተቋሙ አካውንት 1000053091443 በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዋዳ ካምፓስ የውስጥ ገቢ ስም በማስገባት እና እስሊፕ በመያዝ የተዘጋጀውን ሰነድ ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዋዳ (ይ/ ዓለም) ቢ.ኢ.ኮሌጅ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቲም ቢሮ ቁጥር 26 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው የሚወጣበት በ14/04/2017 ዓ.ም ጨረታው የሚከፈትበት በ25/04/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡10 ሰዓት ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዋዳ ቢ.ኢ.ኮሌጅ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቲም በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 25/04/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ድረስ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዋዳ ቢ.ኢ.ኮሌጅ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቲም በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ግዥና ንብረት አስተዳደር ቲም
ስልክ ቁጥር ፡- 046-1-35-00-12
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዋዳ ቢ.ኢ. ኮሌጅ
