Tender Detail

Tender Details

  • Company የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች
  • Address ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ሜክሲኮ ፍሊፕስ ህንጻ አጠገብ የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ላይ አዲስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ???ርድ ቤት ቢሮ ቁጥር 102 : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-515-70-40
  • Websitehttps://www.fsc.gov.et/Home/
  • Deadline30 Dec 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Generators

የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች ከዚህ በታች የተገለፀውን ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች


የግልፅ  ጨረታ  ማስታወቂያ

የግዥ  መለያ  ቁጥር  አ/አ/ከ/ፍ/ቤት/02/2017

 

የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች ከዚህ በታች የተገለፀውን ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። የሚገዛው ዕቃ ዓይነት:- የጀኔሬተር ግዥ

1. የግዥ መለያ ቁጥር አ/አ/ከ/ፍርድ ቤቶች 02/2017

2. ግዥው ግልጽ ጨረታ ነው

3. ጨረ ታ ሰነድ የወጣበት ታህሳስ ወር 2017 ዓ/ም

ተጫራቾች ህጋዊ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ፤ እንዲሁም የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆኑ ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ሰርተፍኬት እና የጨረታ መሳተፊያ ደብዳቤ የሚያቀርቡ ላሸነፉበት እቃ የውል ማስከበሪያ ማስያዝ የሚችሉ እንዲሁም ቋሚ የስራ ቦታ ወይንም ድርጅት ያላቸው ሆነው በቅድመ ምልከታ ወቅት ድርጅታቸውን ወይንም የሥራ ቦታቸውን ማሳየት ፍቃደኛ የሆኑ ከዚህ በፊት በፍርድ ቤቱ ጨረታ አሸንፈው በገቡት ውል መሰረት ግዴታቸውን የተወጡ፡፡

  1. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል  ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ ከግዥ ፈጻሚ የአዲስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ቢሮ 1ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 102 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከላይ ለተገለፁት ዕቃዎች ለተወዳደሩበት ዕቃ በባንክ በተመሰከረለት የክፍያ ትዕዛዝ (C.P.O) ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በቼክ እና በጥሬ ገንዘብ ያስያዘ ከውድድር ውጪ ይደረጋል። ለሚወዳደሩበት ከጠቅላላ ዋጋ 2% ፐርሰንት የጨረታ ማስከበሪያ ማቅረብ አለባቸው ፡፡
  3. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያየ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው። የሚወዳደሩበት ኤንቨሎፕ ላይ የድርጅቱን ስም በመፃፍ እና የድርጅቱን ማኅተም እና ፊርማ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰአት የጨረታው ሳጥኑ ተዘግቶ በዚያው እለት 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ ሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  4. ፍርድ ቤቱ ጨረታውን ለመገምገም የሚጠቀምባቸው መስፈርቶች ጄኔሬተሩን ፍርድ ቤቱ ባወጣው ስፔስፊኬሽን መሰረት እና ጥራት፤ ዋስትና ፣ አነስተኛ ዋጋ እና አጠቃሎ የማቅረብ ጊዜ ግምት ውስጥ ይገባል።
  5. ፍርድ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
  6. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  7. የሚሳተፉ ተወዳዳሪ ድርጅቶች በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች ብቻ መሆን አለባቸው።
  8. ኮፒ እና ኦርጅናል ኤንቨሎፕ በተናጠል (ለየብቻ) በፖስታ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን መስፈርት የማያሟሉ አቅራቢዎች ከጨረታው ውጪ የሚደረጉ ይሆናል፡፡

አድራሻ

ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ሜክሲኮ ፍሊፕስ ህንጻ አጠገብ የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ላይ አዲስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ቢሮ ቁጥር 102 ሲሆን

ስልክ ቁጥር 011-515-70-40

 

የአዲስ  አበባ  ከተማ  ፍርድ  ቤቶች

 

Save Tender