የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ከሚያስተዳድራቸው ቤቶች መካከል 23 ቤቶች ጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብ.ግ.ጨ/አገ/11/04/2017 መግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾችን አወዳድሮ በሽያጭ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
የ3ኛ ዙር ቤቶች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብ.ግ.ጨ/አገ/11/04/2017
- የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ከሚያስተዳድራቸው ቤቶች መካከል 23 ቤቶች ጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብ.ግ.ጨ/አገ/11/04/2017 መግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾችን አወዳድሮ በሽያጭ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
ቤቶቹ የሚገኙበት ጽ/ቤት |
የቤቶቹ ብዛት |
|
1 |
ቅርንጫፍ አንድ ጽ/ቤት |
9 |
|
2 |
ቅርንጫፍ ሁለት ጽ/ቤት |
13 |
|
3 |
ቅርንጫፍ ሦስት ጽ/ቤት |
1 |
|
|
ድምር |
23 |
- ኮርፖሬሽኑ ለሚያከናውነው የቤቶች ሽያጭ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን እና የመወዳደሪያ ተመን ዋጋ በአንድ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ-ሥርዓትና ይህንኑ አስመልከቶ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን መመሪያ መሰረት ነው፡፡
- የተሟላ የጨረታ ሰነዶችን ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች ከታህሳስ 11 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ጥር 02 ቀን 2017 ዓ.ም ቅዳሜን ጨምሮ ባሉት 30 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ ከ 2፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በካሽ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድን ለገሐር በሚገኘው በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት በሚገኘው ዋና የመሰብሰቢ አዳራሽ 1ኛ ፎቅ ለዚሁ ታሽጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በመጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 30ኛው ቀን ወይም ጥር 11 ቀን 2017 ዓ.ም ቀን ከሰዓት 11፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ ሆኖ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ሲ.ፒ.ኦ በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከጨረታው መክፈቻ ዕለትና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጨረታ ሰነዱ ክፍል 1 ላይ በተገለፀበት ቀንና ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ቤቶቹን በአካል ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ማብቂያው ቀን ድረስ በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3:00 እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ቤቶቹ በሚገኙበት አድራሻ ድረስ በመቅረብና ለዚሁ ስራ በሚመደቡ ባለሙያዎች እና በሚወጣው ፕሮግራም መሰረት ቤቶቹን መመልከት ይችላሉ፡፡
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር ፡- 011-8-55-36-12 ወይም 011-8-55-36-17/0911-80-92-63 ወይም 0913-35-62-32 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
ዌብሳይት ፡- website www.fhc.gov.et
ፖ.ሳ.ቁ. Р.О. Box ፡- 299
ፋክስ ቁጥር :- 011-5-54-60-45/ 011-5-52-46-46
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን
