Tender Detail

Tender Details

  • Company የሄንግ ሰን ላንበር ማምረቻ ኃ.የተ.የግል ማህበር
  • Address ኮልፌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 24 ቀበሌ 13 የቤት ቁጥር 1371/108 ተዝንአ ሆስፒታል አካባቢ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ህንጻ 2ኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09 11 42 59 88
  • Website
  • Deadline18 Jan 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Machinery

የሄንግ ሰን ላንበር ማምረቻ ኃ.የተ.የግል ማህበር በፍርድ ቤት የተሰየመው የሂሳብ አጣሪ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት የድርጅቱ ንብረት የሆነውን ስፋቱ 12,420 ካሬ ሜትር ላይ የሰፈረውን የፕላይውድ ማምረቻ ድርጅትና ማምረቻ መሣሪያዎች ሙሉ ንብረቱን ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

የሄንግ ሰን ላንበር ማምረቻ ኃ.የተ.የግል ማህበር


ዘመናዊ  የፕላይውድ  ማምረቻ  ለመሸጥ  የወጣ  የሽያጭ  ጨረታ  ማስታወቂያ  የጨረታ  ቁጥር  001/2017

 

የሄንግ ሰን ላንበር ማምረቻ ኃ.የተ.የግል ማህበር በፍርድ ቤት የተሰየመው የሂሳብ አጣሪ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት የድርጅቱ ንብረት የሆነውን ስፋቱ 12,420 ካሬ ሜትር ላይ የሰፈረውን የፕላይውድ ማምረቻ ድርጅትና ማምረቻ መሣሪያዎች ሙሉ ንብረቱን ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም  በጨረታው  ለመሳተፍ  የሚፈልግ  ማንኛውም  ተጫራች ፡-

  1. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡትን የጠቅላላ ዋጋውን ሁለት በመቶ (2%) CPO (ሲፒኦ) ከዋናው የዋጋ ሰነድ ጋር በማያያዝ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 (ሰላሳ) ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ የድርጅቱ የሂሳብ አጣሪ ቢሮ በሚገኝበት ኮልፌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 24 ቀበሌ 13 የቤት ቁጥር 1371/108 ተዝንአ ሆስፒታል አካባቢ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ህንጻ 2ኛ ፎቅ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን የያዘ የዋጋ ሰነድ (Financial Document) ዋና እና ቅጂ በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት እስከ 31ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ የድርጅቱ የሂሳብ አጣሪ ቢሮ በሚገኝበት ኮልፌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 24 ቀበሌ 13 የቤት ቁጥር 1371/08 ተዝንአ ሆስፒታል አካባቢ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ህንጻ 2ኛው ፎቅ በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ጨረታውን መታዘብ የሚፈልግ ማንኛውም አካል በተገኘበት የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ በወጣ በ31ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት በግልጽ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ በሳምንቱ የእረፍት ቀናት ወይንም በበአላት ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት በግልጽ ይከፈታል፡፡
  5. የጨረታው ውጤት ለአሸናፊውና ለተሸናፊ ተጫራቾች በጽሑፍ በፋብሪካው የውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳና በሒሳብ አጣሪው ቢሮ በር ላይ ይለጠፋል፡፡
  6. አሸናፊው ግለሰብ ወይንም ድርጅት አሸናፊ መሆናቸው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በጨረታው ያሸነፈበትን ዋጋ በ45 ቀናት ውስጥ በመክፈል ንብረቱን ይረከባል፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ጠቅላላ ዋጋውን ከፍሎ ካልተረከበ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ሲፒኦ የሚወረስ ይሆናል፡፡
  7. ተጫራቾች የፋብሪካውን ሁኔታ ፋብሪካው ባለበት ዓለምገና ከተማ ድረስ በመቅረብ ማየት የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  8. ተጫራቾች በሌላ ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተመስርተው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
  9. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 ለተጨማሪ ማብራሪያ በተጠቀሱት ስልክ ቁጥሮች ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፤

 09 11 42 59 88 / 09 11 38 46 24

 

ሄንግ  ሰን  ላምበር  ማኑፋክቸሪንግ  ኃላ/የተ/የግል  ማህበር

 

 

Save Tender