Tender Detail

Tender Details

  • Company የሀረሪ ህዝብ ክልል መንግስት ማረሚያቤቶች ኮሚሽን
  • Address ሀረር ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0256660541
  • Website
  • Deadline28 Dec 2024, 10:30 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Machinery

የሀረሪ ህዝብ ክልል መንግስት ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን በ2017 የበጀት ዓመት የእንጨት ስራ ማእከሉን ማለትም ተግባረ እድ፣ ቤቱን እና ብረታ ብረት ውጤቶች ማምረቻዎችን በውስጡ የሚገኘውን አጠቃላይ የእንጨት ማሽንና ሌሎች ለተግባር እድ አገልግሎት የሚውሉ ንብረቶችን በሙሉ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል።

የሀረሪ ህዝብ ክልል መንግስት ማረሚያቤቶች ኮሚሽን


 

ግልጽ  የጨረታ  መስታወቂያ

 

የሀረሪ ህዝብ ክልል መንግስት ማረሚያቤቶች ኮሚሽን በ2017 የበጀት ዓመት የእንጨት ስራ ማእከሉን ማለትም ተግባረእድ፣ ቤቱን እና ብረታ ብረት ውጤቶች ማምረቻዎችን በውስጡ የሚገኘውን አጠቃላይ የእንጨት ማሽንና ሌሎች ለተግባር እድ አገልግሎት የሚውሉ ንብረቶችን በሙሉ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል። ንብረቶችን በሙሉ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ህጋዊ ድርጅቶች መወዳደር የምትችሉ ሲሆን፤-

  1. ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል ከስራው ጋር ተያያዥነት ያላው እና በ2017 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ፤ የሚፈለግባቸውን የመንግስት ግብር ግዴታ ስለመወጣቱ የሚያመለክት ጊዜው ያላለፈበት ማስረጃ ከሚመለከታቸው ገቢዎች ባለስልጣን እና ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚገልጽ (TIN) ማሰረጃዎችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች በሚመለከታቸው ፍቃድ ሰጪ አካላት በአቅራቢያው የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው ተጫራቾች ብቻ መካፈል ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ዝርዝር የጨረታ ሰነድ በሐረሪ /ህ/ክ/መንግሰት ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ቢሮ የማይመለስ 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፍል መወሰድ ይቻላል።
  4. ተጨራቾች ተቋሙ ባዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ሳጥን ውስጥ እስከ 19/04/2017 ዓ/ም ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ጨረታው በዚህ እለት ማለትም 19/04/2017 ዓ/ም ተዘግቶ 4፡30 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮች በሚገኙበት ይከፈታል።
  6. አሸናፊው ተጨራች ወደ ስራ ሲገባ ከማረሚያ ኮሚሽኑ አላማ አንፃር የሚዘጋጁ የግዴታ ውሎች ይኖሩታል።
  7. የጨረታው አሸናፊ በተመሳሳይ ስራ በመስራት ያስመዘገባቸው ውጤቶች በማስረጃ አስደግፎ ማቅረብ አለበት።
  8. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

    ስልክ ቁጥር - 0256660541

 

የሐ/ህ/ክ/መ/ ማረሚያ  ኮሚሽን

 

Save Tender