በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት፣ በምዕ/ሐረርጌ ዞን የዳሮለቡ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በወረዳው ቀበሌ ውስጥ አዲስ ለሚሰሩት የቀበሌ መሥሪያ ቤቶች የሚውሉ የሕንፃ መሣሪያዎችን መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ በዚህ ጨረታ ለመወዳደር የሚከተለውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
የዳሮለቡ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት፣ በምዕ/ሐረርጌ ዞን የዳሮለቡ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በወረዳው ቀበሌ ውስጥ አዲስ ለሚሰሩት የቀበሌ መሥሪያ ቤቶች የሚውሉ የሕንፃ መሣሪያዎችን መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ በዚህ ጨረታ ለመወዳደር የሚከተለውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
- በሕንፃ መሣሪያ አቅርቦት ዘርፍ የ2017 ዓ.ም ህጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- በዚህ የሥራ ዘርፍ የንግድ የሥራ ፍቃድ መለያ ቁጥር "TIN እና ቫት ተመዝጋቢ መሆን አለበት፡፡
- የጨረታውን ሰነድ በዳሮለቡ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡ መሥሪያ ቤቱ የእቃውን ብዛት እንደ አስፈላጊነቱ ብዛቱን በመጨመር ወይም በመቀነስ ሊያዝ ይችላል፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የዋጋ መጨመር እና ዋጋ ለውጥ ማድረግ እንዲሁም ከተጠየቀው እስፔሲፊኬሽን መቀየር አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ /C.P.O/ 20,000 (ሃያ ሺህ) ለዳሮለቡ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ብለው በመፃፍ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች አድራሻቸውን የድርጅቱን ማህተም በመምታት ኦሪጅናል እና ኮፒ በሰም በተቀባ እና በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ከቆየ በኋላ በ15ኛው የሥራ ቀን ማለትም ከ9/4/2017 እስከ 23/4/2017 ቀን ቆይቶ ከጠዋቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታውን አያደናቅፈውም፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ የዳሮለቡ ወ/ገ/ፅ/ቤት በስልክ ቁጥር 0255570025 መደወል ይችላሉ፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ውል ከመሥሪያ ቤቱ ጋር በመፈራረም እስከ መሥሪያ ቤታችን የዳሮለቡ ወ/ገ/ፅ/ ቤትግምጃ ቤት በራሱ ትራንስፖርት መጫኛ እና ማውረጃ ጨምሮ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- አነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች ይበረታታሉ፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
የዳሮለቡ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት
