በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ግዥ አስተዳደር ቡድን የ2017 በጀት አመት በሁለተኛ ዙር ጨረታ ከዚህ በታች በሎት የተጠቀሱትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ግዥ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ግዥ አስተዳደር ቡድን የ2017 በጀት አመት በሁለተኛ ዙር ጨረታ ከዚህ በታች በሎት የተጠቀሱትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት 1 የቋሚ እቃ ግዥ
ሎት 2 የሆቴል አገልግሎት ግዥ
ሎት 3 የደንብ ልብስ
ሎት 4 የጋራዥ አገልግሎት
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከተ.ቁ 1-3 የተዘረዘሩትን በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ፣
- የግብር ከፋይነት (tin number) ማቅረብ የሚችሉ፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት1. 5000 (አምስት ሺ ብር)፣ ሎት2. 3000 (ሦስት ሺ ብር)፣ ሎት.3 5000 (አምስት ሺህ ብር)፣ ሎት4. 5000 (አምስት ሺ ብር) በCPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ 250.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ ብር) በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ሆኖ የጨረታው ሰነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት ሃይሌ ጋርመንት ላፍቶ አደባባይ በሚገኘው የክፍለ ከተማው ህንጻ ዘጠነኛ ፎቅ በመቅረብ መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያውን ዋጋ በመሙላት እና ከተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ኦሪጅናልና ኮፒ በማሸግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) የስራ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ለመልካም ሥራ አፈጻጸም (ለውል ማስከበሪያ) ያቀረቡትን ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጫራቾች ለሚኖራቸው ጥያቄ በስልከ ቁጥር 011 8 34-27-15 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ግዥ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት
