በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፓሬሽን ትራንስፖርት መሠረተ ልማት ኮንስትራክሽን ዘርፍ የሳላይሽ-ኦሞ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ የተለያዩ መጠን ያላቸው ያገለገሉ ባዶ የአስፋልት በርሜሎች ባዶ የዘይት በርሜሎች እና የተለያየ አምፒር ያላቸው ባትሪዎች ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፓሬሽን ትራንስፖርት መሠረተ ልማት ኮንስትራክሽን ዘርፍ የሳላይሽ-ኦሞ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ የተለያዩ መጠን ያላቸው ያገለገሉ ባዶ የአስፋልት በርሜሎች ባዶ የዘይት በርሜሎች እና የተለያየ አምፒር ያላቸው ባትሪዎች ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
- ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ከሚፈለገው አገልግሎት የተዛመደ የ2016 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰርተፍኬት እና ግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት በማቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር) የኢትዮጵያ ብር የፕሮጀክታችን የሂሳብ ቁጥር ECWC Head Office Control Accont (100053673733117) ገቢ በማድረግ እና ገቢ ያደረጉበት የባንክ ደረሰኝ ይዘው በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጥዋቱ 2፡30 ጀምሮ ለአስራ አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ሳላይሽ-ኦሞ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ግዥ ፣ አቅርቦትና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነድ ውስጥ የተመለከቱትን መስፈርቶች አሟልቶ ከፍተኛ ዋጋ የሚያቀርበው ተጫራች ሲሆን የጨረታ ሰነዱ የተዘጋጀው በአማርኛ ቋንቋ ነው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ጋንችሬ በሚገኘው ግዥ ፣ አቅርቦትና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ የታሸገ የጨረታ ሠነድን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቹኋል።
- ተጫራቾች ከሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ ከ 10 በመቶ (10%) ያላነሰ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /CPO/ ወይም በባንክ ዋስትና ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የኢንሹራንስ ቦንድ ተቀባይነት የለውም።
- የጨረታው ሳጥን መዝጊያ ቀን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከዋለበት ቀን ተቆጥሮ የሚዘጋ ይሆናል።
- የጨረታው ሳጥን መክፈቺያ ቀን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ይሆናል።
- ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሠረት ጨረታውን ማቅረብ አለባቸው ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀን ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጨረታ ሰነዱ ላይ በሚጠቀሰው ቀንና ሰዓት ጋንችሬ በሚገኘው ግዥ፣ አቅርቦትና ንብረት አስተዳደር ቢሮ የጨረታ ሠነዱን ከገዙበት ቦታ ይሆናል፡፡
- ፕሮጀክቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡
ለበለጠ መረጃ – 09-25-06-56-90, 09-35-73-58-12
የሳላይሽ-ኦሞ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት
