የሸኖ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በሸኖ ከተማ ውስጥ ለሚሰራው የኮሪደር ልማት የሚውል ኤክስከቫተር ከነጃክ ሀመር እና 16 ሜትር ክዩብ እና ከዚያ በላይ ይዘት ያላቸው ገልባጮች በጨረታ አወዳድሮ በኪራይ ለማሰራት ይፈልጋል።
በኦሮሚያ ክልል የሸኖ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የሸኖ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በሸኖ ከተማ ውስጥ ለሚሰራው
የኮሪደር ልማት የሚውል ፡-
- ኤክስከቫተር ከነጃክ ሀመር፡-
- 16 ሜትር ክዩብ እና ከዚያ በላይ ይዘት ያላቸው ገልባጮች በጨረታ አወዳድሮ በኪራይ ለማሰራት ይፈልጋል።
ስለዚህ በስራ ዘርፉ የዘመኑን ግብር የከፈላችሁ፣ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላችሁ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT 15% ተመዝጋቢ የሆናችሁ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN ያላችሁ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመገቡ መሆናቸውን የምስከር ወረቀት ማቅረብ የምትችሉ፤ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በሸኖ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በግንባር በመቅረብ ዝርዝር መጠይቆችን የያዘውን ሰነድ በማይመለስ ብር 800 በካሽ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ በዝርዝር የተመለከተውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በካሽ ወይም ሲፒኦ "CPO " ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ22ኛው ቀን በ8፡00 ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ተወካዮች በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የስራ ቀን ካልሆና በቀጣይ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፤
- ጨረታውን ያሸነፈ ድርጅት ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ውሉን ፈጽሞ ስራውን የመጀመር ግዴታ አለበት፡፡
- ተጨማሪ መግለጫዎች ተዘጋጅቶ በሚሸጠው በጨረታ ሰነዱና በ“Specification ላይ በዝርዝር ይገኛል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ /አማራጭ /ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ :- ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ በሚወስደው መንገድ 78 ኪሎ ሜትር ሸኖ ከተማ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስ.ቁ፡- 0910093362 በመደወል ጠይቆ መረዳት ይቻላል፡፡
በኦሮሚያ ክልል የሸኖ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
