በገቢዎች ሚኒስቴር የምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ፅ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የሰራተኞች ሰርቪስ የመኪና ኪራይ አገልግሎት እና የጣት አሻራ ማሽን እና የሰራተኞች የሰዓት መቆጣጠሪያ መተግበሪያ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል።
በገቢዎች ሚኒስቴር የምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ፅ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ምስ/አ/አ/አ/ግ/ከ/ቅ/ፅ/ቤት MOR EAST OPEN BID 04/2017
በገቢዎች ሚኒስቴር የምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ፅ/ቤት
የ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል
|
ሎት |
የአገልግሎት አይነት |
|
1 |
የሰራተኞች ሰርቪስ የመኪና ኪራይ አገልግሎት |
|
2 |
የጣት አሻራ ማሽን እና የሰራተኞች የሰዓት መቆጣጠሪያ መተግበሪያ |
በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል። በመሆኑም ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልግ ድርጅት የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ
- የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተተ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆኑን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው
- የዘመኑን ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ (ክሊራንስ) ማቅረብ የሚችል
- የጨረታ ማስከበሪያ 2% በባንክ በተመሰከረ ሲፒአ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረት የባንክ ጋራንቲ
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መገናኛ አካባቢ የቀድሞ ለም ሆቴል በስተቀኝ ኮሜት ህንፃ ቁጥር 2 የሚገኘው በገቢዎች ሚኒስቴር የምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ፅ/ቤት 8ኛ ፎቅ 806 ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ በአካል ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሀሳቡን ዋናውን እና ኮፒውን በማስያዝ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21/04/2017 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታውም በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፅ/ቤቱ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 8-06 ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% በማስያዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር ፡- 011-6-67-47-31
በገቢዎች ሚኒስቴር የምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ፅ/ቤት
