የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የግብርና ምርት ማሳደጊያዎች አቅርቦት ዘርፍ የተለያዩ ኬሚካሎችን እና ፈሳሽ ማዳበሪያዎችን ከአዲስ አበባ፣ ከአዳማ፣ ከሞጆ እና ከአሰላ ወደ ተለያዩ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች እና ሽያጭ ጣቢያዎች በዘርፉ የተሰማሩ እና ፍቃድ ያላቸውን ትራንስፖርተሮች በጨረታ አወዳድሮ ማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡
የትራንስፖርት ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የግብርና ምርት ማሳደጊያዎች አቅርቦት ዘርፍ የተለያዩ ኬሚካሎችን እና ፈሳሽ ማዳበሪያዎችን ከአዲስ አበባ፣ ከአዳማ፣ ከሞጆ እና ከአሰላ ወደ ተለያዩ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች እና ሽያጭ ጣቢያዎች በዘርፉ የተሰማሩ እና ፍቃድ ያላቸውን ትራንስፖርተሮች በጨረታ አወዳድሮ ማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳድር ይችላሉ፡፡
- የደረቅ ጭነት አጓጓዥነት የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው፣
- የመንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣን የምዝገባ ፍቃድ ያለው፣
- በውል በሚቀመጠው መሰረት ድርጅቱ በሚፈልግ ጊዜ 50 ኩንታል መጫን የሚችል አይሱዙ ወይም 100 ኩንታል የሚጭን ኤፍ ኤስ አር ማቅረብ የሚችል፣
- ተጓጉዞ የሚጠናቀቅበት ጊዜ በሚያዝ ውል በሚቀመጥ ጊዜ ውስጥ ድርጅቱ ማጓጓዝ በሚፈልግበት ጊዜ እና ኬሚካሉ ለጭነት እንደተዘጋጀ በፅሁፍ ወይም በስልክ ባሳወቀ በ3 (ሶስት) ቀን ውስጥ 50 ኩንታል መጫን የሚችል አይሱዙ ወይም 100 ኩንታል የሚጭን ኤፍ ኤስ አር በማቅረብ ኬሚካሎቹንና ፈሳሽ ማዳበሪያዎችን በተረከበበት ሁኔታ በጥንቃቄ ለተላከለት ቅ/ፅ/ቤት ወይም ሽያጭ ጣቢያ ማስረከብ የሚችል፣
- ኬሚካል እና ፈሳሽ ማዳበሪያ 50 ኩንታል በሚጭን አይሱዙና 100 ኩንታል በሚጭን ኤፍ ኤስ አር ተሽከርካሪ ሙሉ ጭነት ወደ ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች እና ሽያጭ ጣቢያዎች የሚያጓጓዝበትን ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ የሚችል፣
- ለጨረታ ማስረከቢያ ዋስትና እንዲሆን ብር 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ሲፒኦ (ባንክ ጋራንቲ) ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት፡፡
- የጨረታው ሳጥን የጨረታ ማስታወቂያ ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ክፍት ይሆናል፡፡ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዘርፍ ፅ/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
- በጨረታው ውጤት በማስታወቂያ በተገለጸ በ5 ቀናት ውስጥ የጨረታው አሸናፊ የውል ጊዜው እስኪጠናቀቅ የሚቆይ 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (ባንክ ጋራንቲ) በማስያዝ ቀርቦ ውል መፈረም አለበት፡፡
- ዘርፉ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በሥራ ሰዓት በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የግብርና ምርት ማሳደጊያዎች አቅርቦት ዘርፍ አቃቂ ቃሊቲ ቀበሌ 12/13 ከቃሊቲ ጉምሩክ ወደ ጅንአድ በሚያስገባው መንገድ ገባ ብሎ ባለው የዘርፉ ቢሮ በመምጣት በቢሮ ቁጥር G-4 በማይመለስ 200 ብር ክፍያ በመፈጸም መግዛት ይችላል፡፡
- ከጨረታ ሰነዱ ውጪ የሚቀርብ የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ተቀባይነት የለውም፡፡
- የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ የሚቀርቡት የዋጋ ዝርዝሮች ስርዝ ድልዝ ካላቸው ተቀባይነት የላቸውም፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ ወይም ግልፅ ያልሆነ ጉዳይ ካለ በስልክ ቁጥር 0114425639 ወይም 0114425660 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ግብርና ምርት ማሳደጊያዎች አቅርቦት ዘርፍ
