Tender Detail

Tender Details

  • Company የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሚልሻ ጽ/ቤት
  • Address ሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት ፊት ለፊት ትንሽ አለፍ ተብሎ ባለው ግቢ ውስጥ ቢሮ ቁጥር 5 : ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046 212 4273
  • Website
  • Deadline28 Dec 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Office Machines And Computers

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሚልሻ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሮኒስ ማለትም ዲስክቶፕ ፕሪንተር ፤ ላፕቶፕ እና L.C.D ፡ ፕሮጀክተር በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሚልሻ ጽ/ቤት


ግልፅ  የጨረታ  ማስታወቂያ

 

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሚልሻ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሮኒስ ማለትም ዲስክቶፕ ፕሪንተር ፤ ላፕቶፕ እና L.C.D ፡ ፕሮጀክተር በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህ  መሠረት

  1. በግብር ከፋይነት ተመዝግበው የአቅራቢነት ሠርተፍኬት ግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ሆነው የዘመኑን ግብር የከፈሉ በጨረታ መሳተፍ የሚችሉበትን የግዜ ገደብ የሚገልፅ ማስረጃ በመያዝ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነድ በመግዛት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛ ተከታታይ በሥራ ቀናት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሚልሻ ጽ/ቤት ግዥ ፋይናንስና ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ የውል ማስከበሪ ቢድ ቦንድ በሕጋዊ ባንከ በተረጋገጠ ወይም በስተጀርባ ህጋዊ የባንክ ማህተም ያረፈበት ቼክ ወይም ሲፒኦ በማዘጋጀት ኦርጅናልና ኮፒ ፖስታዎችን ለየብቻ በታሸገ ኤንቬሎፕ ውስጥ በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከጨረታ መመሪያ ጋር አባሪ ተደርጎ ይያያዛል፡፡
  3. ይህ ጨረታ በ16ኛው በሥራ ቀን ከጧቱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከ4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ። 16ኛ ቀን ቅዳሜና ዕሁድ ከሆነ ወይም በዓል ቀን ከሆነ የጨረታ መክፈቻ ዕለት በተጠቀሰው ሰዓት በሚቀጥለው ሥራ ቀን ይሆናል።
  4. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ዝርዝር ሰነድ ላይ ስምና አድራሻ በግልፅ በመሙላት በማህተምና በፊርማ ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡ አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም ።
  5. ተጫራቾች መመሪያ ባለማከበራቸው የሚፈፀም ማንኛውም ስህተት ሀላፊነቱ የተጫራቾች ይሆናል ።
  6. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ

ሀዋሳ  ከተማ  ከፍተኛ  ፍ/ቤት  ፊት  ለፊት  ትንሽ  አለፍ  ተብሎ  ባለው  ግቢ  ውስጥ  ቢሮ  ቁጥር  5 ስልክ ቁ. 0462124273

 

ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሚልሻ ጽ/ቤት

 

Save Tender