Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የእህልና ቡና ንግድ ሥራ ዘርፍ
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 4 66 47 45
  • Website
  • Deadline22 Dec 2024, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Food And Beverage

በኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የእህልና ቡና ንግድ ዘርፍ መጠኑ 1,774.53 ኩ/ል 1ኛ ደረጃ ምስር በአዳማ መጋዘን የሚገኝ ሲሆን ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ላላቸው ድርጅቶች ብቻ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የእህልና ቡና ንግድ ሥራ ዘርፍ


ምስር እህል ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የእህልና ቡና ንግድ ዘርፍ መጠኑ 1,774.53 ኩ/ል 1ኛ ደረጃ ምስር በአዳማ መጋዘን የሚገኝ ሲሆን ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ላላቸው ድርጅቶች ብቻ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

 

ተ.ቁ

እህሉ የሚገኝበት ቦታ

የእህል ዓይነት

መጠን በኩል

የጥራት ደረጃ

እህሉ የሚገኝበት መጋዘን

እህሉ የሚውለው አገልግሎት

1

አዳማ

ምስር

1,774.53

1ኛ ደረጃ

9

ለሰው ምግብነት

ድምር

 

1,774.53

 

 

 

 

 

በዚህ  መሰረት  በጨረታው  ለመሳተፍ  የሚፈልጉ  ተጫራቾች፡-

  1. ተጫራቾች አግባብነት ያለው በጥራጥሬ በጅምላና ችርቻሮ ንግድ ወይም ላኪነት የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
  2. ምስሩን ተጫርተው መግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀናት እህሉ በሚገኙበት መጋዘን በአዳማ መጋዘን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00- 6፡00 እና ከሰዓት 7፡00 - 10፡30 እና ቅዳሜ ከ 2፡00 - 6፡00 ማየት ይችላሉ፤
  3. ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ከዋናው መ/ቤት (አዲስ አበባ) ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 10፡30 እንዲሁም ቅዳሜ ከ2፡00 እስከ 6፡00 የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታው ውጤት እንደታወቀ ተመላሽ የሚሆን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /Bid Bond/ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ከመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር በዘርፉ ስም (የእህልና ቡና ንግድ ዘርፍ ወይም Grain and Coffee Trading Business Unit) በሚል ብቻ የተሰራ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ አለባቸው፡፡
  5. የሚጫረቱበትን ዋጋ በሰነድ ላይ ባለው የዋጋ መሙያ ሰንጠረዥ ያለስርዝ ድልዝ በመሙላት በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. በግልፅ የማይነበብ ትክክለኛውን የዋጋ አቀራረብ ሥነ ስርዓት ያልተከተለ የመጫረቻ ሠነድ ውድቅ የሚደረግ ሲሆን የዋጋ ማቅረቢያ ሠነድ ላይ ስርዝ ካለው የተጫራቹን አጭር ፊርማ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
  7. ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ በመሙላት ሰነዳቸውን በኤንቨሎፕ በማሸግ የጨረታ ቁጥር 03/2017 በማለት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ለአስር የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በአስራ አንደኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 004 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ አስራ አንደኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ቀጣይ ባለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
  8. አሸናፊ ተጫራች ውል ሲፈርም የውል ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋውን 10% ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ መቻል አለበት፣
  9. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ለአስር የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በአስራ አንደኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 004 ይከፈታል፡፡ አስራ አንደኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ቀጣይ ባለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
  10. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚደርሱ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
  11. የጨረታ አሸናፊ የሆነ ድርጅት እህሉን ተረክቦ ወደሚፈልግበት ቦታ በራሱ የሚያጓጉዝ ይሆናል ፡፡
  12. ዘርፉ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
  13. ለበለጠ  መረጃ  በስልክ  ቁጥር፡- 011 4 66 47 45 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

በኢትዮጵያ  የንግድ  ሥራዎች  ኮርፖሬሽ  ( የእህልና  ቡና  ንግድ  ሥራ  ዘርፍ )

 

Save Tender