በኢፌዴሪ ጉምሩክ ኮሚሽን ሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት 11 ሰው እና ከዚያ በላይ በወንበር መያዝ የሚችል ተሽከርካሪ ከዚህ በታች በቀረበው መስፈርት መሰረት በጨረታ ቁጥር 007/2017 አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል።
በጉምሩክ ኮሚሽን የሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በኢፌዴሪ ጉምሩክ ኮሚሽን ሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት 11 ሰው እና ከዚያ በላይ በወንበር መያዝ የሚችል ተሽከርካሪ ከዚህ በታች በቀረበው መስፈርት መሰረት በጨረታ ቁጥር 007/2017 አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል።
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የሥራ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር አጠናቀው ስለመክፈላቸው ማስረጃ (ክሊራንስ)፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት የሚያሳይ ማስረጃዎችን አደራጅተው ማቅረብ አለባቸው::
- 11 ሰው እና ከዚያ በላይ በወንበር መያዝ የሚችል ተሽከርካሪ ቀኑን ሙሉ አገልግሎት መስጠት የሚችል መሆን ይኖርበታል፡፡
- ደረጃ 2 እና ከዚያ በላይ የብቃት ማረጋገጫ ያለው ተሽከርካሪ ማቅረብ የሚችል እና የብቃት ማረጋጋጫ ማስረጃውን ከጨረታ ሰነድ ጋር የሚያያይዝ ወይም ሲጠየቅ ማቅረብ የሚችል፤
- ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ እና የተጫራቾች መመሪያ የማይመለስ ብር 200 በመክፈል ወደ ዲላ በሚወስደው ዋና አስፋልት ከጨርቃ ጨርቅ ፊት ለፊት ባለው ላቀች ህንፃ ቢሮ ቁጥር 101 የሀብት አስተዳደር ስራ ሂደት በመምጣት መውሰድ ይችላሉ ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ብር 20,000.00 (ሀያ ሺህ ብር) በሲ.ፒ.አ ያስያዙበትን ማስረጃ ወይም መመሪያው በሚፈቅደው መሰረት ዋስትና ማቅረብ የሚችሉ ::
- ተጫራቾች በግዢ ኤጀንሲ ድረ ገፅ ላይ የተመዘገቡ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ካለ፤
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ቴክኒከ ሰነድ እና የፋይናንሻል ዋናውንና አንድ ኮፒ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ፖስታ ለብቻ ለብቻ በማድረግ ቢሮ ቁጥር 101 አንደኛ ፎቅ ሀብት አስተዳደር ስራ ሂደት ለዚሁ ጨረታ ተበሎ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሣጥኑ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወደ ዲላ በሚወስደው ዋና አስፋልት ከጨርቃ ጨርቅ ፊት ለፊት ያለው ላቀች ህንፃ ምድር ላይ በሚገኘው ሻይ ክበብ ውስጥ ይከፈታል።
ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::
ማብራሪያ ቢያስፈልግዎት የስ.ቁ 046 212 6502/046 2219 675 ይጠቀሙ::
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጉምሩክ ኮሚሽን ሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት
