የሰሜን ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ የግብርና ግብአት አቅርቦትና የገጠር ፋይናንስ አገልግሎት ቡድን ለ2017/18 የምርት ዘመን አገልግሎት የሚውል የአፈር ማዳበሪያ ዳፕ 90731 ዩሪያ 84179 በድምሩ 174,909.5 ኩ/ል (አንድ መቶ ሰባ አራት ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠኝ) ኩ/ል በዞናችን ባሉ ጀምበርና ፋና ዩኒየኖች በስራቸው ላሉ 83 መሰረታዊ ማህበራት መጋዘን ድረስ ለማጓጓዝ ብቃት ያላቸውና የትራንስፖርተሮች ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ውል ከተፈፀመበት ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 30/2017 ዓ/ም ድረስ የሚቆይ የትራንስፖርተር አገልግሎት ግዥ መፈፀም ይፈለጋል።
የሰሜን ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ
የጨረታ ማስታወቂያ
የሰሜን ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ የግብርና ግብአት አቅርቦትና የገጠር ፋይናንስ አገልግሎት ቡድን ለ2017/18 የምርት ዘመን አገልግሎት የሚውል የአፈር ማዳበሪያ ዳፕ 90731 ዩሪያ 84179 በድምሩ 174,909.5 ኩ/ል (አንድ መቶ ሰባ አራት ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠኝ) ኩ/ል በዞናችን ባሉ ጀምበርና ፋና ዩኒየኖች በስራቸው ላሉ 83 መሰረታዊ ማህበራት መጋዘን ድረስ ለማጓጓዝ ብቃት ያላቸውና የትራንስፖርተሮች ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ውል ከተፈፀመበት ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 30/2017 ዓ/ም ድረስ የሚቆይ የትራንስፖርተር አገልግሎት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው ግዴታዎች
- በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር /ቢሮ የታደሰ የዘመኑ የንግድ ስራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፤
- ቫት ተመዝጋቢ የሆነና መረጃ ማቅረብ የሚችል፤
- የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊኬት ቲን ነምበር ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
- በጨረታው ላይ የሚሳተፍ ማንኛውም ተጫራች ከ70 ኩ/ል በላይ የሚጭኑ ተሽከርካሪዎች የሚያቀርቡ ከሆነ ከፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ተመዝግበው የተደራጁ ሆነው በዘመኑ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ከ70 ኩ/ል በታች ከሆነ በክልል ትራንስፖርት ቢሮ ተመዝግበው የተደራጁ ሆነው በዘመኑ የታደሰ የብቃት ማቅረብ የሚችል።
- የተሽከርካሪ ዝርዝር/ ተ/ቁ፤ የሰሌዳ ቁጥር፤ የመኪናው ጤንነትና የመጫን አቅም የሚያስረዳ ከፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ወይም ከክልል መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ የተሰጠ ወቅታዊ የታደሰ የምዝገባ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ 1 እና 6 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
- የሚጓጓዘውን የአፈር ማዳበሪያ አይነት፤ መጠን፤ ርቀት በኪሎ ሜትር ዝርዝር መግለጫ ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በእያንዳንዱ ዩኒየን ስም የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመግዛት ሰነዱን ሰሜን ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ የክፍያ የስራ ቡድን ቢሮ ቁጥር 50 ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ/ ለሚወዳደሩበት የአገልግሎቱን ጠቅላላ ዋጋ 2% በሚወዳደሩበት ዩኒየን ስም ማስያዝ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአንድ ፖስታ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በማሸግ በሰሜን ወሎ ዞን ግብርና ግብአቶች አቅርቦት ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰአት ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ማለትም 22/4/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የሁለቱንም ዩኒየኖች ሰነድ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በማስገባት የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈተው በእለቱ በ22/4/2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይሆናል።
- የተሽከርካሪ የባለቤትነት ማስረጃ ኮፒ ማያያዝ ይኖርበታል።
- የጨረታ ማስከበሪያው ቢል ቦንድ ከሆነ ከህጋዊ ቋንቋ ተርጓሚ በማስተርጎም ማቅረብ ይኖርበታል።
- መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 331 2751 በመደወል አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ።
የሰሜን ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ
ወልድያ
