Tender Detail

Tender Details

  • Company ዴቨሎፕመንት ኤንድ ሪሊፍ አሶሴሽን
  • Address አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከ የሚገኘው ከቱሉ ዲምቱ አደባባይ ወደ ዓለምባንክ በሚወስደው መንገድ ቱሉ ሞል ህንጻ 6ኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0902330910
  • Website
  • Deadline04 Jan 2025, 12:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Vehicle

ድርጅታችን ዴቨሎፕመንት ኤንድ ሪሌፍ አሶሴሽን በሽያጭ መለያ ቁጥር ዲ/አር/ኤ/-ሽያጭ/001/2017 ያገለገለ ተሽከርካሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፤

ዴቨሎፕመንት ኤንድ ሪሊፍ አሶሴሽን


የጨረታ  ማስታወቂያ

 

ድርጅታችን ዴቨሎፕመንት ኤንድ ሪሌፍ አሶሴሽን በሽያጭ መለያ ቁጥር ዲ/አር/ኤ/-ሽያጭ/001/2017 ያገለገለ ተሽከርካሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፤

በዚህ መሠረት

 

የሰሌዳ ቁጥር

የእቃው አይነት

ሻንሲ ቁጥር

የሞተር ቁጥር

የሞተሩ ጉልበት

ብዛት

መነሻ ዋጋ

ዕድ 35-3980

ቶዮታ ሃይሉክስ (ባለ ሁለት ጋቢና ፒካፕ 2008 ሞዴል)

MROFR22G78656313

2KD-7613764

2986

1

2,900,000

 

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ፣

  1. ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ አዲስ አባባ ከሚገኘው አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ከቱሉ ዲምቱ አደባባይ ወደ ዓለም ባንከ በሚወስደው መንገድ ሞል ህንፃ 6ኛ ፎቅ ላይ ከሚገኘው ከድርጅቱ ቢሮ ለሽያጭ መለያ ቁጥር ዲ/አር/ ኤ-ሽያጭ/ 001/2017 ብር 500 (አምስት መቶ ብር መክፈል ይችላሉ
  2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት በጨረታ ዶክመንት ውስጥ በተጠቀሰው ቦታ ድረስ በመሄድ የሚወዳደሩባቸውን ተሽከርካሪ መመልከት ይችላል።
  3. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ተሽከርካሪ በመነሻ ጠቅላላ ዋጋ 20% የሚሆነውን ለጨረታ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሚያቀርቡት ጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ እና በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ። የሚዘጋጀው CPO በዴቨሎፕመንት ኤንድ ሪሊፍ አሶሴሽን ስም መሆን አለበት ።
  4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ ሲያቀርቡ በታሸገ ፖስታ ሆኖ በፖስታው ላይ የተጫራቾች ሙሉ ስም ፈርማ እና አድራሻ በማይለቅ ቀለም በመፃፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች ከመጫረቻ ሰነድ ጋር መቅረብ የሚጠበቅባቸው ማስረጃዎች እድሜ 18 አመት እና ከዚያ በላይ መሆኑን እና ማንነቱን የሚገልፅ መታወቂያ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት ።
  6. የሽያጭ መለያ ቁጥር ዲ/አር/ኤ-ሽያጭ/001/2017 ታህሳስ 26 ቀን 2017 ከጠዋቱ በ6:00 ተዘግቶ በእለቱ በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዴቨሎፕመንት ኤንድ ሪሊፍ አሶሴሽን ቢሮ ይከፈታል።
  7. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ተሽከርካሪ የሽያጭ ውል ከተዋዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ቀናት ውስጥ ጠቅላላ ከፍያ በመፈፀም ማንሳት ይኖርበታል።
  8. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ተሸከርካሪ በሚያነሱበት ወቅት የማጓጓዣ ክፍያዎች በራሳቸው የሚሸፈን ይሆናል
  9. በየበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0902330910/0911991762 በመደወል ማነጋገር ይቻላል።
  10. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለማብራሪያ እና ጥያቄ የሻጭ አድራሻ የድርጅቱን ቢሮ አዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከ የሚገኘው ከቱሉ ዲምቱ አደባባይ ወደ ዓለምባንክ በሚወስደው መንገድ ቱሉ ሞል ህንጻ 6ኛ ፎቅ ወለል ላይ ነው።

ስልክ ቁጥር 0902330910/0913338681

 

ዴቨሎፕመንት  ኤንድ  ሪሊፍ  አሶሴሽን

 

Save Tender