የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ግብር ከፋይ የሚጠበቅባቸውን የታክስ ዕዳ በታክስ ህጉ በተፈቀደው የጊዜ ገደብ ባለመክፈላቸው በታክስ አከፋፈል አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 41 በተሠጠው ስልጣን መሠረት ከጀነሲስ ፋርማስ ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተያዙ 3 ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት
የግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 01/2017
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ
የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ግብር ከፋይ የሚጠበቅባቸውን የታክስ ዕዳ በታክስ ህጉ በተፈቀደው የጊዜ ገደብ ባለመክፈላቸው በታክስ አከፋፈል አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 41 በተሠጠው ስልጣን መሠረት ከጀነሲስ ፋርማስ ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተያዙ 3 ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም
- በግልጽ ጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ማንነቱን የሚገልጽ የነዋሪነት መታወቂያ (ፓስፖርት) ኮፒ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ በግልጽ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ የግልጽ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00 ሰዓት - 11፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00 - 6፡00 ሰዓት ከቴሌ ከፍ ብሎ ቅ/ጽ/ቤቱ አዲሱ ባስገነባው ህንጻ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403 ከግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቢሮ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይኖርባታል።
- በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ንብረቶች የሰጡትን ዋጋ 1/10ኛውን ብቻ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) በገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት ስም (Ministry of Revenue Adama Branch Office) በባንከ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት ሰነድ ገዝተው መጫረት ይችላሉ፡፡
|
ተ.ቁ |
የመ/ቤቱ ስም |
ለጨረታ የቀረበው የንብረት ዓይነት |
የንብረቶቹ መመልከቻ ጊዜ |
የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
ገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅርንጫፍ |
የተለያየ ሞዴል ያላቸው ተሽከርካሪዎች |
ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት |
ማስታወቂያው በጋዜጣ ወጥቶ 15 ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ቀጥሎ ባለው 16ኛ ቀን 3፡45 ተዘግቶ በዚያው ቀን በ4፡00 ሰአት ይከፈታል። |
- ጨረታው መክፈቻ ቦታ:- በገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት ከቴሌ ከፍ ብሎ ባስገነባው አዲሱ ህንጻ 4ኛ ፎቅ በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳዳር ቢሮ ቁጥር 403 ሲሆን ተጫራቶች/ ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም ታዛቢዎች ባሉበት ይከፈታል፡፡
- የግልጽ ጨረታው መክፈቻና መዝጊያ 16ኛው ቀን የመ/ቤቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን የግልጽ ጨረታው መክፈቻና መዝጊያ ቀን ይሆናል፡፡
- ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙት (CPO) ከሚከፈሉት ዋጋ ጋር እንደ አስፈላጊነቱ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የግልጽ ጨረታ ኮሚቴው መረጃውን አጣርቶ እንደጨረሰ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
- የተሸከርካሪ ጨረታ ለሚያሸንፉ ተጫራቾች ከስመ-ንብረት ዝውውር ገር ተያያዥነት ያላቸውን ወጪዎች (የቦሎና ሌሎች ተጓዳኝ ወጪዎች) ሻጭን አይመለከትም፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀናት ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ ቅ/ጽ/ቤቱ በሚሰጠው አድራሻ ገቢ በማድረግ ሀብት/ንብረት መረከብ ይኖርበታል፡፡
- ከላይ በተ.ቁ 9 በተግለጸው ቀናት ውስጥ ከፍያውን ገቢ በማድረግ ንብረታቸውን ያልተረከቡ ተጫራቾች የግልጽ ጨረታው ተሠርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በ CPO ያስያዙት የዋስትና ገንዘብ ለመ/ ቤቱ ገቢ ሆኖ ንብረቱ ተቆጥሮ በቀጣይ በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
- ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ የግልጽ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ
ስልከ ቁጥር፡- 022-211-1873/022-211-1728 እና 022-211-0762 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
ገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት
