በኢትዮጵያ ኤሌክትሪከ አገልግሎት የነቀምት ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጽ/ቤት በያዘው በጀት ዓመት በሎት 1 የከባድ ተሽከርካሪ ጎማ 12*20 እና በሎት 2 የቀላል ተሽከርካሪ ጎማ 7.50*16 ከነ ሙሉ አክሰሰሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ነቀምት ሪጅን ጽ/ቤት
በሎት 1 የከባድ ተሽከርካሪ ጎማ 12*20 እና በሎት 2 የቀላል ተሽከርካሪ 7.50*16 ከነ ሙሉ አክሰሰሪው ግዥ ለመፈጸም የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር EEU/NREU/NCB/01/2017
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪከ አገልግሎት የነቀምት ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጽ/ቤት በያዘው በጀት ዓመት በሎት 1 የከባድ ተሽከርካሪ ጎማ 12*20 እና በሎት 2 የቀላል ተሽከርካሪ ጎማ 7.50*16 ከነ ሙሉ አክሰሰሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ማንኛውም በዘርፉ የተሠማራችሁ ግለሠብ ወይም ድርጅት መወዳደር የሚችሉ ሲሆን፤ በዚህ ጨረታ ላይ ለመሣተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡና በመስኩ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና፣ በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጄንሲ https://epg.ppa.gov.et ድረ ገጽ ላይ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፣
- የጨረታ ሠነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ታህሳስ 14 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ነቀምት ሪጅን መ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 300 ድረስ በመቅረብ የማይመለስ ብር 500.00 / አምስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ EEU Nekemt region ተከፋይ የሆነ በሎት 1 የከባድ ተሽከርካሪ ጎማ 12*20 ከነሙሉ አክሰሰሪ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) እና በሎት 2 ለቀላል ተሽከርካሪ ጎማ 7.50*16 ጎማ ብር 40,000.00 /አርባ ሺህ ብር/ በባንከ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት ባንክ ጋራንቲ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ቴክኒካል ኮፒና ኦርጅናል ለየብቻ በማድረግ እንዲሁም ፋይናንሻል ኮፒና ኦሪጅናል ለየብቻ በማድረግ ሲፒኦ /CPO/ ኦሪጅናል ቴክኒካል ሰነድ ውስጥ በመክተት አራቱንም በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ በማድረግ እስከ ተጠቀሰው የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት ድረስ በኢትዮጵያ ኤሌከትሪክ አገልግሎት ነቀምት ሪጅን ነቀምት ከተማ ኒው ጀነሬሽን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ አጠገብ በሚገኘው ህንፃ 3ኛ ፎቅ ሪጅን ሰፕላይ ቼይን ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 30 ድረስ በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው ታህሳስ 14 ቀን 2017 ዓ.ም 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8:30 ላይ ይከፈታል፡፡
- ሪጅኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልከ ቁጥር 0576602015/0911570832/091156406 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ነቀምት ሪጅን ጽ/ቤት
ነቀምት
