Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኩታበር ወረዳ ፍ/ቤት
  • Address አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0914068901
  • Website
  • Deadline13 Dec 2024, 9:30 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Office Machines And Accessories

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኩታበር ወረዳ ፍ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በጋዜጣ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኩታበር ወረዳ ፍ/ቤት


ግልጽ  የጨረታ  ማስታወቂያ

የጨረታ  ቁጥር  197/2017

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኩታበር ወረዳ ፍ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በጋዜጣ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል:: ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ሎት 1 አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች ሎት 2 ቋሚ እቃ ፣ ሎት 3. የቢሮ ማሽነሪ ፤ ሎት 4. ህትመት ሎት 5. የደንብ ልብስ፣ ሎት 6. አላቂ የፅዳት እቃዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ፡-

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው::
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ/ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የሚገዙ እቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (Specfication) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በኩታበር ወረዳ ፍ/ቤት ግዥ/ፋ/ን/አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 10 ከ/03/03/2017 ዓ.ም ጀምሮ መግዛት ይችላሉ።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲ.ፒ.ኦ. ለሚወዳደሩበት ብር ወይም ለሚሰራው ስራ ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኢ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ /በቼክ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡንም ኦርጂናልና ኮፒ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በኩታበር ወረዳ ፍ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 10 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ቀን ከ30/03/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 18/04/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 10 በቀን 18/04/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ይከፈታል ተጫራቾች ለእቃው ዓይነትም ሆነ መጠን በጨረታው በሙሉ ወይም በከፊል መሳተፍ ይችላሉ፡፡ ሆኖም አንድ ተጫራች በአንድ ሎት ውስጥ ከተዘረዘሩት የእቃ ዓይነቶች መካከል ከፋፍሎ መሠረት አይችልም፡፡
  11. መ/ቤቱ ጨረታውን በሎት ድምር ወይም በነጠላ ዋጋ የማወዳደር መብቱ የተጠበቀ ነው:: መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈለጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0914068901 ወይም 0920794336 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

 

በአማራ  ብሔራዊ  ክልላዊ  መንግስት  የኩታበር  ወረዳ  ፍ/ቤት

Save Tender