ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ሀገር በቀል የሆነ በኢፌዴሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ተመዝግቦ በተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ በመስራት ላይ የሚገኝ ድርጅት ነው:: ድርጅቱ ከዚህ በታች ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል ::
Mary Joy Ethiopia (ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ)
የጨረታ ማስታወቂያ
ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ሀገር በቀል የሆነ በኢፌዴሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ተመዝግቦ በተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ በመስራት ላይ የሚገኝ ድርጅት ነው:: ድርጅቱ ከዚህ በታች ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል ::
1ኛ. ቶዮታ ካሪና አውቶሞቢል ጃፓን 4 ሰው የሚይዝ ሞዴል 1988 ቦታው አስኮ ሜሪ ጆይ ህክምና ማዕከል ግቢ ውስጥ
2ኛ. ቶዮታ ሎንግ ቤዝ ጃፓን 11 ሰው የሚይዝ ሞዴል 1987 ቦታው አስኮ ሜሪ ጆይ ህክምና ማዕከል ግቢ ውስጥ
3ኛ. ቶዮታ ላንድ ክሩዘር 1H2 6 ሰው የሚይዝ ሞዴል ቦታው ሀዋሳ ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ፕሮጀከት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ
4ኛ. ሱዙኪ ቪታራ 3 ሰው የሚይዝ ሞዴል - ቦታው ሀዋሳ ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ
- በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ከላይ በተጠቀሰው የድርጅቱ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት ዘወትር በስራ ሰዓት በቦታው በመሄድ ማየት፤
- ማንኛውም ተጫራች ተሽከርካሪውን ካየ በኋላ የሚገዛበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ባየበት ቦታ ለጽ/ቤቱ ማስገባት ይኖርበታል ፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ወደ ጽ/ቤት ሲመጡ ብር 4,000.00 ማሲያዝ አለባቸው፡፡
- ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአምስት (5) የስራ ቀናት ውስጥ በድርጅቱ ጽ/ቤት በማየት ሰነዱን ማስገባት ይቻላል፡፡
- ጨረታ የሚከፈተው ድርጅቱ ለተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቀድሞ የሚያሳውቅ ይሆናል ፡፡
- ተጫራቾች የመንግስት ታክስ እና ከግብር ለማጓጓዣ የሚስፈልጉትን ወጪዎች በሙሉ አሸናፊው ተጫራች ይሸፍናል፡፡
- መኪናዎቹም አሁን ባለበት ሁኔታ ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ያስረክባል፡፡
- ተጫራቾች የመንግስት ታክስ፣ ግብር እና ስም ዝርዝር ጋር የተያያዙ ወጪዎችን እራሳቸው ይሸፍናሉ፡፡
- ንብረቶችን ለመጫን እና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉትን ወጪዎች በሙሉ አሸናፊ ተጫራች ይሸፍናል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማስታወሻ ፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-668-67-93 ወይም 0962009422 በመደወል መጠየቅ ይችላል፡፡
ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ
