በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ሸዋ ዞን መስተዳድር የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ የደነባ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ለቄራ አገልግሎት የሚውል ግንባታ ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ሸዋ ዞን ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን የደነባ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ሸዋ ዞን መስተዳድር የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ የደነባ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ለቄራ አገልግሎት የሚውል ግንባታ ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው እና የግንባታ ዋጋ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ካለምንም ስርዝ ድልዝ ዋጋቸውን ሞልተው በክብ ማህተም ሙሉ ስማቸውንና አድራሻቸውን መግለጽ አለባቸው፡፡
- የስራ ዓይነትና ዝርዝር ከጨረታ ሰነድ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከላይ በተገለጸው መሰረት የማይመስስ 300.00 /ሶስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ የተጭበረበረ ሲፒኦ /የባንከ ዋስትና/ ማቅረብ በህግ ያስጠይቃል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 3:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የበዓል /የዕረፍት/ ቀን ከሆነ በተከታዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ከደረጃ 8 GC በላይ የግንባታ ፍቃድ ያላቸው መሆን አለበት፡፡
- አሸናፊ የጨረታው ዋጋ ብር 3000.00 /ሶስት ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ 2% ዊዝሆልዲንግ ታክስ ከአጠቃላይ ዋጋ ታስቦ ይከፍላል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ ከተረጋገጠ በኋላ 25% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
- ለማንኛውም መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0912410949/0921745220/0925242028/0953984609 ላይ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ሸዋ ዞን ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን የደነባ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት
