የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ የከተማ ቦታን በሊዝ ለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 በፊደል ተራ ከሀ እስከ "ሠ" በተዘረዘረው መሰረት ለመኖሪያ እና ንግድ አገልግሎት የተዘጋጁ ቦታዎችን በግልፅ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ
የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
- የጨረታ ቁጥር፡ ደማ/01/2017
- የጨረታ ዙር፣ 1ኛ
- የጨረታ ዓይነት፣ መደበኛ
- የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ የከተማ ቦታን በሊዝ ለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 በፊደል ተራ ከሀ እስከ "ሠ" በተዘረዘረው መሰረት ለመኖሪያ እና ንግድ አገልግሎት የተዘጋጁ ቦታዎችን በግልፅ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከአገልግሎት አቅርቦት ተጠሪ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በስራ ስራ ሰዓት መግዛት የሚቻል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ በ10ኛው ቀን የጨረታ ሰነድ የሚሸጠው እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ብቻ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ብቻ ይሆናል።
- የጨረታ ሳጥን የሚታሸገው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣበት በ11ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ነው፡፡
- ቦታውን መጎብኘት ለሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጉብኝት ፕሮግራም በውስጥ ማስታወቂያ የምናሳውቅ ይሆናል።
- ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት በመምሪያው ግቢ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡ 11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ስለጨረታው ዝር ዘርዝር ማብራሪያ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.አ የተጫረቱበትን የቦታ ስፋት በቦታው የመነሻ ዋጋ በማባዛት የሚገኘውን ውጤት ከሀያ በመቶ ያላነሰ በዝግ አካውንት በማስገባት በባንክ የተመሰከረለት ሰነድ ከዋጋ እና የሃሳብ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል።
- በጨረታው ለተሸነፉ ተወዳዳሪ ያስያዙ ከያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተመላሽ የሚደረገው የጨረታው አሸናፊ ከተረጋገጠበት ከሚቀጥለው ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ይሆናል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ
