Tender Detail

Tender Details

  • Company የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት (FDRE Refugees and Returnees Service)
  • Address የእንቁላል ፋብሪካ አደባባይን ሳይሻገሩ ከፌዴራል ፖሊስ ክበብ ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 813 21 93
  • Websitehttps://rrs.et/
  • Deadline11 Dec 2024, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Vehicle tire

በስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ስር የሚገኘው የስደት ተመላሾች መልሶ ማቋቋሚያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት የተሸከርካሪ ጎማ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት (FDRE Refugees and Returnees Service)


የጨረታ  ማስታወቂያ

 

በስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ስር የሚገኘው የስደት ተመላሾች መልሶ ማቋቋሚያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት የተሸከርካሪ ጎማ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ተጫራቾች -

  1. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤ በጨረታ ለመወዳደር የሚያስችል ክሊራንስ፤ ሕጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና በጨረታ ለመሳተፍ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያሳይ የምዝገባ የምስከር ወረቀት ያላቸው መሆን አለባቸው::
  2. የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጀምሮ ባሉት 5 የሥራ ቀናት ውስጥ በሥራ ሰዓት በፕሮጀከት ጽ/ቤቱ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 የስራ ቀናት ውስጥ በጨረታ ሰነዱ ላይ የእቃዎችን ዋጋ ዝርዝር በመሙላትና የጨረታ ማስከበሪያ በአገልግሎቱ የስደት ተመላሾች መልሶ ማቋቋሚያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት የግዢ ከፍል ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ እስከ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ5ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ 5ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ቅዳሜና እሁድ የመ/ቤቱ የሥራ ቀናት አይደሉም፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ የሚያቀርቡትን አጠቃላይ ዋጋ 2% የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት Refugee and Returnee Service በሚል የተዘጋጀ የባንክ ማዘዣ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. አገልግሎቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- እንቁላል ፋብሪካ፣ ከፌዴራል መኮንኖች ከበብ ፊት ለፊት

ለተጨማሪ  ማብራሪያ  በስልክ  ቁጥር ፡- 011-8-72-13-76 ወይም 011-8-72-15-37 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

የስደተኞችና  ተመላሾች  አገልግሎት  የስደት  ተመላሾች

መልሶ  ማቋቋሚያ  ፕሮጀክት  ጽ/ቤት

Save Tender