Tender Detail

Tender Details

  • Deadline25 Dec 2024, 10:30 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Labour Outsourcing Services

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለኢንዱስትሪና ግብርና ውጤቶች ንግድ ዘርፍ የፓርኪንግ አስተባባሪ፤ የጥበቃ ሠራተኛ፣ የጥበቃ ተራ አስተባባሪ፣ የጽዳት ሰራተኛ እና አትክልተኛ ሰራተኞችን የውጭ አገልግሎት ከሚሰጡ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡ ኢንሥኮ-ማዕከል ግዥ ብ/ግ/ጨ/07/2017

 

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለኢንዱስትሪና ግብርና ውጤቶች ንግድ ዘርፍ የፓርኪንግ አስተባባሪ፤ የጥበቃ ሠራተኛ፣ የጥበቃ ተራ አስተባባሪ፣ የጽዳት ሰራተኛ እና አትክልተኛ ሰራተኞችን የውጭ አገልግሎት ከሚሰጡ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታ ላይ መወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መመዘኛዎች ማሟላት አለባቸው፡፡

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ለ2016/2017 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ፈቃድ ወይም ጨረታው እስከሚከፈትበት ቀን ድረስ ሊያገለግል የሚችል የንግድ ስራ ፈቃድ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፤ የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፤ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ወቅታዊ ክሊራንስ ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት፤ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የብቃት ሰርትፍኬት እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን እነዚህ ሰነዶች በቴክኒካል ፕሮፖዛል ፖስታ ውስጥ ታሽገው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የፋይናንሻል ሰነዳቸውን ለብቻ በፖስታ በማሸግና የፋይናንሻል ሰነድ መሆኑን በመግለጽ ማቅረብ አለባቸው።
  2. ተጫራቾች ከላይ የተገለጹትን ሰነዶች ከጨረታ ሰነድ ማቅረቢያው ቀነ ገደብ በፊት ማቅረብ አለባቸው።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 450.00 (አራት መቶ አምሳ ብር) በመክፈል ከታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00-6፡00 ሰዓት እንዲሁም ከሰዓት ከ7፡00-10፡30 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00-6፡00 ሰዓት ድረስ ብሎክ 1 ቢሮ ቁጥር 206 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡ (አድራሻው ከስር ተገልጿል፡፡)
  4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን እስከ ጨረታው መዝጊያ ዕለት እስከ ታህሳስ 16 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ፣ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡ ኢንሹራንስ ቦንድና ቼክ ተቀባይነት የላቸውም፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው በቴክኒካል ፕሮፖዛል ፖስታ ውስጥ ወይም ለብቻው ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
  6. ተጫራቾች የቴክኒክ መወዳደሪያ ሰነዳቸውንና ዋጋ የሞሉበትን የጨረታ መወዳደሪያ ሀሳባቸውን በግልጽ ከፋፍለው የቴክኒክና የፋይናንስ ሰነድ በማለት በተለያየ ኤንቨሎፕ ለየብቻ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ጨረታው ታህሳስ 16 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋናው መስሪያ ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  8. ከዋና የመወዳደሪያ ሀሳብ (ኦሪጅናል) በተጨማሪ የሚፈለጉ ኮፒዎች ብዛት 1 (አንድ)፣
  9. አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ መጠን 10 ፐርሰንት /አስር ፐርሰንት/ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ስም አሰርተው ውሉን የሚፈጽሙ ይሆናል፡፡
  10. ኮርፖሬሽኑ ጨረታውን በከፊልም ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብረቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለማንኛውም ማብራሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡

በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን

ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

ደብረዘይት መንገድ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ ፊት ለፊት

ስልክ ቁጥር 011 416 73 45/011 466 9336

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

 

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን

Save Tender