በአማራ ብሄራዊ ከልላዊ መንግስት የአብክመ ጤና ቢሮ የደቡብ ወሎ ዞን የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለ2017 ዓ.ም በጀት አመት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውሉ የግንባታ እና ጥገና ማቴሪያሎች፣ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች ፣ አላቂ የፅዳት እቃ፣ የህትመት ውጤቶች፣ የአልሙኒየም በርና መስኮት ስራ፣ የጣውላ ሼልፍ ስራ እና ብረታ ብረት ስራ የህሙማን ለማሰራት፣ የደንብ ልብስ ግዥ ለአንድ ጊዜ ግዥ እና ለአንድ አመት የሚቆይ የህሙማን አልባሳት አጠባ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ከልላዊ መንግስት የአብክመ ጤና ቢሮ የደቡብ ወሎ ዞን የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለ2017 ዓ.ም በጀት አመት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውሉ የግንባታ እና ጥገና ማቴሪያሎች፣ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች ፣ አላቂ የፅዳት እቃ፣ የህትመት ውጤቶች፣ የአልሙኒየም በርና መስኮት ስራ፣ የጣውላ ሼልፍ ስራ እና ብረታ ብረት ስራ የህሙማን ለማሰራት፣ የደንብ ልብስ ግዥ ለአንድ ጊዜ ግዥ እና ለአንድ አመት የሚቆይ የህሙማን አልባሳት አጠባ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- ተጫራቾች ለተወዳደሩበት የአቅርቦት አይነት የተዛመደ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግዥው መጠን ከ200,000 በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- ተጫራቾች በጨረታው · ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተገለፁትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታው ኦሪጅናል ሰነዶች ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የስራ ቀናት ከሆስፒታሉ ግዥ ክፍል የማይመለስ 200 ብር በመክፈል ማግኘት ይችላሉ::
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ አይነት ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% ሲፒኦ ብቻ በማሰራት ከኦርጅናሉ የጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ ሙሉ ስምና አድራሻ ጽፎ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም ኦሪጅናል ሰነዱ እና ፎቶ ኮፒ ለብቻው ሙሉ አድራሻው ተጽፎ እና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ በጥንቃቄ ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡
- የጨረታው ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በማስታወቂያ በወጣ 15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነድ ሽያጭ ተሸጦ በቀጣዩ የስራ ቀን ከቀኑ 4:00 ታሽጎ በእለቱ 4፡30 ይከፈታል፡፡
- ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ሆስፒታሉ በሚጋብዘው የቴክኒከ ባለሙያ ተረጋግጦ እቃው ገቢ ይሆናል፡፡
- ሆስፒታሉ በሚያቀርበው ናሙና እቃው ገቢ ይሆናል፡፡
- አስፈላጊ መረጃ መጠየቅ ከፈለጉ በሆስፒታሉ ስልክ ቁጥር 033117670 መደወል ይችላሉ።
የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
