በአብከመ የኦሮ/ብ/ዞን የደዋ ጨፋ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በወረዳው ስር ለሚገኘዉ መስኖና ቆላማ አካባቢ ጽ/ቤት በመደበኛ ካፒታል በጀት በወረዳችን በ2017 ዓ.ም የሰላማ ቆላ መስኖ ፕሮጀከት ግንባታ ለማከናወን የተለያዩ የፋብሪካ ግብዓቶች ማለትም ሲሚንቶ ቆርቆሮ ፌሮ ብረት ወዘተ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊዎች ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአብከመ የኦሮ/ብ/ዞን የደዋ ጨፋ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በወረዳው ስር ለሚገኘዉ መስኖና ቆላማ አካባቢ ጽ/ቤት በመደበኛ ካፒታል በጀት በወረዳችን በ2017 ዓ.ም የሰላማ ቆላ መስኖ ፕሮጀከት ግንባታ ለማከናወን የተለያዩ የፋብሪካ ግብዓቶች ማለትም ሲሚንቶ ቆርቆሮ ፌሮ ብረት ወዘተ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊዎች ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾቾ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን መስፈርቶቹም፡-
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የምዝገባ የምስክር ወረቀት (Tin No) አብረው ማያያዝ የሚችሉና ከ 200,000 ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ዘርዝር ሰነድ የያዘ ከኦሮ/ብ/ዞ/ደ/ጨ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 11 በመቅረብ የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ዕለት ጀምሮ ለ15 /ለአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ገዝተዉ በመሙላት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ኢንቨሎፕ በማሸግ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ዕለት ጀምሮ በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 4፡00 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጐ በዚህ ቀን 4፡30 የሚከፈት መሆኑን እየገለጽን ሆኖም የመክፈቻው ዕለት ባዕላት ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀናት በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾቾ ለሞሉት ለጠቅላላ የጨረታ መጠን ላይ በብር 35,000/ሰላሳ አምስት ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ CPO እና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፤፤
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት መረጃ ኦርጅናልና ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣ ለበለጠ መረጃ የተጫራቾችን መመሪያ ላይ መረዳት ይቻላል ወይም በስልከ ቁ 0335540225/0294 መደወልና መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- አሸናፊዎች ያሸነፋትን እቃ ደዋ ጨፋ ወረዳ ገን/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፣ በጨረታ አሸናፊ የሆኑት ተጫራቾች ውል ካልገቡ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ በሙሉ ለመንግስት ገቢ ይሆናል::
- መ/ቤቱ ጨረታዉን በሎትም ሆነ በነጠላ ማወዳደር ይችላሉ፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
በአብክመ የኦሮ/ብ/ዞን ቦደዋ ጨሩ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
