በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን በዳራ ማሎ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት የተለያዩ ያገለገሉ እና አገልግሎታቸውን ያቆሙ የዋ ሞተር ሳይክሎች፣ ጀነሬተሮች፣ ትራክተር ከነተሳቢው፣ ትራክተር ባለ ሞተር በሰው እጅ የሚገፋ ካዜናዎች፣ ያገለገሉ የመኪና ጎማዎች እና የተለያዩ ብረታብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በጋሞ ዞን ዳራማሎ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን በዳራ ማሎ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት የተለያዩ ያገለገሉ እና አገልግሎታቸውን ያቆሙ ሞተር ሳይክሎች፣ ጀነሬተሮች፣ ትራክተር ከነተሳቢው፣ ትራክተር ባለ ሞተር በሰው እጅ የሚገፋ ካዜናዎች፣ ያገለገሉ የመኪና ጎማዎች እና የተለያዩ ብረታብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለዚህ ጨረታውን ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 (ሃያ አንድ) ተከታታይ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 300 (ሦስት መቶ ብር) ብቻ በወረዳ ገቢዎች ባለስልጣን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመክፈል የከፈሉበትን 2ኛ ኮፒ በመያዝ ለፋይናንስ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 9 በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይቻላል።
የጨረታ ማስከበሪያ ከየትኛውም ህጋዊ ባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ጥሬ ብር 20,000 (ሃያ ሺህ) ብር ማስያዝ /ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው የሚከፈተው በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ታሽገው 5፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡ የተሽከርካሪዎች የሥም ዝውውር እና ሌሎች ወጪዎች በአሸናፊ ተጫራች ይሸፈናል፡፡ አሸናፊ ተጫራች ያሸነፈበት ገንዘብ በመክፈል በአምስት ቀናት ውስጥ ንብረቱን ማንሳት አለበት፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻችን ፡- ከወላይታ ሶዶ ከተማ ወደ ጎፋ መስመር 93 ኪ.ሜ ላይ እንገኛለን፡፡
በጋሞ ዞን ዳራማሎ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
