Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Press Agency (የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)
  • Address አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-1-56-98-69
  • Websitehttps://press.et/
  • Deadline20 Dec 2024, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Transportation Service And Cargo

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2017 በጀት ዓመት በጥሪ ማዕከል የተደገፈ የትራንስፖርት አገልግሎት በውል ለአንድ ዓመት በዘርፉ ከተሠማሩ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም ፡- በሥራ ዘርፉ የተሠማሩና ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በውድድሩ መሳተፍ ይችላሉ፡፡

Ethiopian Press Agency (የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)


በድጋሚ  የወጣ  ብሔራዊ  ግልጽ  የጨረታ  ማስታወቂያ

የጨረታ  ማስታወቂያ  ቁጥር ፡- ኢፕድ 004/2017

 

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2017 በጀት ዓመት በጥሪ ማዕከል የተደገፈ የትራንስፖርት አገልግሎት በውል ለአንድ ዓመት በዘርፉ ከተሠማሩ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።  ስለሆነም ፡- በሥራ ዘርፉ የተሠማሩና ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በውድድሩ መሳተፍ ይችላሉ፡፡

ይህም ፡-

  1. በሥራ ዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት እና በመንግስት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
  2. ዕጩ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ግዥውን አስመልክቶ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት ግዥ ቡድን በአካል በመምጣት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት በመውሰድ የሚወዳደሩበትን ዝርዝር ዋጋ ከቫት ጋር በመሙላት የጨረታ ሰነዱን በ4 በታሸገ የተለያየ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናሉንና ኮፒዎቻቸውን ለየብቻ በማቅረብ ጉዳዩን አስመልክቶ በተዘጋጀው በፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት ግዥ ቡድን በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  3. ዕጩ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ብር 120,000.00 (አንድ መቶ ሃያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ/ቢድ ቦንድ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  4. ጨረታው ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሠዓት ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  5. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 011-1-56-98-69 ወይም

Email:procurement@press.et

አድራሻ ፡ አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ፊት ለፊት

 

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

Save Tender