Tender Detail

Tender Details

  • Company የከታ ሙዱጋ ገበሬዎች ሁለገብ የህብረት ሥራ ዩኒዬን
  • Address , Phone: 0917821364
  • Website
  • Deadline20 Dec 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Transportation Service And Cargo

የከታ ሙዳጋ ገበሬዎች ሁለገብ የህብረት ሥራ ዩኒዬን ለ 2017/18 የምርት ዘመን የሚውል የአፈር ማዳበሪያ በዞኑ ውስጥ ከሚገኙ ማዕከላዊ መጋዘኖች ለማህበራት ለማጓጓዝ በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውን ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉትን የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የጭነት አገልግሎት መግዛት ይፈልጋል፡፡

የከታ ሙዱጋ ገበሬዎች ሁለገብ የህብረት ሥራ ዩኒዬን


የአፈር ማዳበሪያ ለማጓጓዝ የወጣ

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የከታ ሙዳጋ ገበሬዎች ሁለገብ የህብረት ሥራ ዩኒዬን ለ 2017/18 የምርት ዘመን የሚውል የአፈር ማዳበሪያ በዞኑ ውስጥ ከሚገኙ ማዕከላዊ መጋዘኖች ለማህበራት ለማጓጓዝ በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውን ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉትን የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የጭነት አገልግሎት መግዛት ይፈልጋል፡፡

የሚጓጓዘው የአፈር ማዳበሪያ አይነትና ብዛትም የሚከተለው ይሆናል፡፡

* ዳፕ (DAP) 50,000 ± 25% ኩንታል፤

* ዮሪያ (UREA) 30,000 ± 25% ኩንታል፤

* በድምሩ 80,000 ± 25% ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ

በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፤
  3. በአቅራቢነት የተመዘገቡ እና ሰርተፍኬቱን ማቅረብ የሚችሉ፤
  4. የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ከፈዴራል ወይም ከክልል መንገድ ትራንስፖርት ማቅረብ የሚችሉ፤
  5. ያላቸውን የደረጃ ጭነት መኪናዎች ዝርዝር ታርጋ ቁጥር ከነተሳቢ እና ሊብሬ (የንብረት ባለቤትነት ማርጋገጫ) ማቅረብ የሚችሉ፤
  6. ተጫራቾች የታክስ ክሊራንስ ማረጋገጫ ከገቢዎች ጽ/ቤት ማቅረብ አለባቸው::
  7. ተጫራቾች ከ1-7 ተራ ቁጥር የተገለጹትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማመሳከር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ማራገፊያ ጣቢያዎች የመንገድ ሁኔታና ርቀት ከውድድሩ በፊት አስቀድመው ማየታቸውን በጽሁፍ ማረጋገጥ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ጨረታውን ካሸነፉና ውል ከፈጸሙ በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም የመንገድ ሁኔታ ችግር ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  9. ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ ዝርዝር መሰረት የአፈር ማዳበሪያ የሚጓጓዝበትን ዋጋ ለአንድ ኩንታል የአንድ ኪሎ ሜትር የማጓጓዣ ዋጋ በግልፅ ሳይደለዝ በተቀመጠው ሠንጠረዥ ላይ መሙላት አለባቸው::
  10. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 1.5% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከህጋዊ ባንከ የተመሰከረለት CPO በድርጅቱ ስም ማስያዝ አለባቸው::
  11. ተወዳድረው የሚያሸንፉ ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው በጽሁፍ ከተገለጸላቸው ጀምሮ በ15 ቀን ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ድምር 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና፤ ኦሪጅናል እና ፎቶኮፒ ሊብሬ በማቅረብ ውል መዋዋል ይኖርባቸዋል፡፡
  12. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 500 ብር በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ጅማ ከተማ በሚገኘው የዩኒዬኑ ጽ/ቤት ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
  13. የጨረታው ማስከበሪያ ሰነድ ከ 60 ቀን በኋላ ለተጨማሪ 28 ቀን ጸንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
  14. የጨረታው ሰነድ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ለየብቻ ተዘጋጅቶ ኦሪጅናሉን እና ፎቶ ኮፒውን በተለያየ ፖስታ አስገብተው በማሸግ ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን፣ ኦሪጂናል የቴክኒካል ማስረጃዎችን ከCPO ጋር በአንድ ፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ “ኦሪጅናል ቴክኒካል ፣ ኮፒ የቴክኒካል ማስረጃዎችን ደግሞ በሌላ ፖስታ በማሸግ የታሸገበት ፖስታ ላይ "ኮፒ ቴክኒካል” በማለት፤ እንዲሁም የዋጋ ዝርዝር ማቅረቢያ ሰነዶችን ኦሪጂናሉን በአንድ ፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ ”ኦርጅናል ፋይናንሻል"፣ ኮፒ የዋጋ ዝርዝር ማቅረቢያ ሰነዶችንም ለብቻ በማሸግ “ ኮፒ ፋይናንሻል" በማለት በጥቅሉ በአራት ፖስታ ታሽጎ የሚቀርብ ሲሆን በተጨማሪም በእያንዳንዳቸው ፖስታ ላይ የተወዳዳሪው ስም, አድራሻ, ፊርማ እና በማህተም በማረጋገጥ ሁሉንም የታሸጉ ፖስታዎች በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ አድርጎ በማሸግ የተወዳዳሪው ስምና አድራሻ፣ የዩኒዬኑ ስም ተጽፎበት በማህተም በማረጋገጥ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  15. የጨረታው ሣጥን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4:15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል።
  16. ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

         ለተጨማሪ ማብራሪያ ቀጥሎ ባሉት የስልከ ቁጥሮች ወይም በአካል ቀርበው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

ስልክ ቁጥር 0917821364

 

የከታ ሙዱጋ ገበሬዎች ሁለገብ የህብረት ሥራ ዩኒዬን

Save Tender