በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ፊርኒቸር ኤሌክትሮኒክስ የቢሮ መገልገያ የፅህፈት መሣሪያዎችንና የፅዳት ዕቃዎች፣ የሞተር ሣይክል የተለያዩ ፕሪንተር ቀለሞች በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ፊርኒቸር ኤሌክትሮኒክስ የቢሮ መገልገያ የፅህፈት መሣሪያዎችንና የፅዳት ዕቃዎች፣ የሞተር ሣይክል የተለያዩ ፕሪንተር ቀለሞች በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት፣
- የንግድ ፍቃዳቸው የምዝገባ ሠርተፍኬታቸውን ለ2017 ዓ/ም ያሳደሱ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣
- ተጨማሪ እሴት ታከስ የተመዘገቡ ጨረታውን በሲዳማ ከልል ጤና ቢሮ በመቅረብ ለግዥ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከቢሮ ቁጥር 27 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ CPO 2% የጨረታ ዋስትና በባንከ የተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ ማስያዝ የሚችል፤ ሆኖ በሂሳብ ስሌት ምርመራ የተገኘው የጨረታ ዋስትና ከቀረበው ዋጋ በታች ሆኖ ከተገኘ ከጨረታ ውጪ ያስደርጋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዳቸውን ቴክኒካልና ፋይናንሻል ለእያንዳንቸው አንድ ኦርጂናል ሁለት ኮፒ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው፤ በመሆኑም ከዚህ በላይ ከተገለጸው ውጪ የሚያቀረቡ ከውድድር ውጪ ያስደርጋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነድ በተጠየቀው መሠረት ማቅረብ መቻል አለበት፣
- ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን 6፡00 ሰዓት ድረስ የግ/ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ክፍል በተዘጋጀው ጨረታ ሣጥን በማስገባት በተጠቀሰው ሰዓት ይታሸጋል፣ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት ይከፈታል፤ 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፤
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0462125847 ይጠይቁን።
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ
