የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ባኦሜትሪክ እቴዳንስ መቆጣጠሪያ ማሽን፣ ዲጅታል ሳይነጅ እና ፈሳሽ ናይትሮጂን ማሽን መለዋወጫ ዕቃ ህጋዊ ተጫራቾችን በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 05/2017
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ባኦሜትሪክ እቴዳንስ መቆጣጠሪያ ማሽን፣ ዲጅታል ሳይነጅ እና ፈሳሽ ናይትሮጂን ማሽን መለዋወጫ ዕቃ ህጋዊ ተጫራቾችን በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች ፡-
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ፣ ተጨማሪ እሴት ታከስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆነ፤ ጨረታ መሳተፍ የሚችልና የምዝገባ ምሰክር ወርቀት ማቅረብ የሚችል/የሚትችል።
- ጨረታው በዚህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት ቀን) ተከታታይ ቀናት የጨረታ ዶክመንት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) ባንክ በማስገባት ከመ/ቤቱ ግዥ/ፋይ/ንብ/አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ከጎርጋዳ ሰፈር ከፍ ብሎ ኦሞ ባንክ ህንፃ አጠገብ ባለው ህንፃ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 16 በአካል ሆነ በተወካዮቻቸዉ አማካይነት መግዛት ይቻላል፡፡
- በየዘርፉ የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና /Bank GAURANT/ ወይም የክፍያ ማዘዣ(CPO) ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ከቴክኒካል ሰነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት፡፡
- አሸናፊ ሆኖ የሚመረጠው ተጫራች የዉል ማስከበሪያ የሚሆን ገንዘብ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ያሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ አለበት።
- ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሰረት ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን ሰነድ በተለያየ ፖስታ በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመፃፍ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን (ተከታታይ ቀናት) ከጠዋቱ 2፡30 እሰከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ግዥ /ፋይ/ንብ⁄ አስ/ዳይሬከቶሬት ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በአስራ ስድስተኛዉ ቀን ሰነድ መሸጥና መግዛት አይቻልም፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ 6፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም::
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው፡፡
- መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የድርጅት ህጋዊ ማህተም ሳያደርግ የቀረበ ተጫራች ከውድድሩ ዉጪ ይሆናል፡፡
- የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለፀዉ ቦታና ሰዓት ይሆናል፡፡
- የሰነድ ማስገቢያ ከመጨረሻዉ ቀንና ሰዓት በኋላ የሚመጡ አመልካቾች ተቀባይነት አይኖራቸዉም።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0916108360/0916070057 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
አድራሻ ፡- ከጎርጋዳ ሰፈር ከፍ ብሎ ኦሞ ባንከ ህንፃ አጠገብ ባለው 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 16 እንገኛለን፡፡
በሲዳማ ብሔራዊ ክልልላዊ መንግስት እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ
