የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የቆሻሻ ፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎት እና የከብቶች ቀለብ ወይም መኖ አቅርቦት ግዥ በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በዚህም መሰረት በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሁሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ (NCB009/2017) እና NCB010/2017
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የቆሻሻ ፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎት እና የከብቶች ቀለብ ወይም መኖ አቅርቦት ግዥ በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በዚህም መሰረት በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሁሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ህጋዊና የዘመኑ ግብር ከፍለው የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ በመንግስት ግዥ ላይ ለመሳተፍ የተመዘገቡበት የአቅራቢነት የምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የግብር ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
|
ተ.ቁ |
የግዥው ዓይነት |
የጨረታው መለያ ቁጥር |
የጨረታ ማስከበሪያ (በብር) |
የጨረታው መዝጊያ |
የጨረታው መክፈቻ |
||
|
ቀን |
ሰዓት |
ቀን |
ሰዓት |
||||
|
1 |
የቆሻሻ ፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎት ግዥ |
NCB 009/2017 |
10,000.00 |
በ16ኛው ቀን |
5፡30 |
በ16ኛው ቀን |
5፡45 |
|
2 |
የከብቶች ቀለብ ወይም መኖ ግዥ |
NCB 010/2017 |
10,000.00 |
በ16ኛው ቀን |
8፡00 |
በ16ኛው ቀን |
8፡15 |
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ሸጎሌ በሚገኘው በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ግዥ ዲፓርትመንት ቢሮ ድረስ በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ከዚህ በታች በሰንጠረዡ መሠረት በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ስም ሞልተው ከኦርጅናል የመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው የመወዳደሪያ ሰነዶች ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ኦሪጅናል እና አንድ ኮፒ በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ ለየብቻው አሽገው የጨረታውን ስምና ቁጥር በመፃፍ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ተከታታይ ቀን ጀምሮ በሰንጠረዡ መሠረት በኮርፖሬሽኑ ግዥ ዲፓርትመንት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኃላ የሚመጡ ተጫራቾች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሸጎሌ በሚገኘው በኮርፖሬሽኑ ዋናው መ/ቤት ግዥ ዲፓርትመንት ቢሮ ውስጥ ይከፈታል ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የመንግስት የሥራ ቀን ካልሆነ ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር ሁኔታዎች ከጨረታ ሰነዱ ላይ የሚያገኙ ሲሆን ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር 011-517-25-21 ደውለው ወይም በአካል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታው በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን
