በማዕከላዊ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የሆሳዕና ዲስትሪከት ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በበሌሳ ከቤቾ ዳርሻ ዶዕሻ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ለሾርሜ ድልድይ ግንባታ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ መጠን ያላቸው ድልድይ ግንባታ ብረቶችን ከብቁ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለሥልጣን የሆሣዕና ዲስትሪክት ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ሆሣዕና ዲስትሪክት 003-2017
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የሆሳዕና ዲስትሪከት ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በበሌሳ ከቤቾ ዳርሻ ዶዕሻ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ለሾርሜ ድልድይ ግንባታ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ መጠን ያላቸው ድልድይ ግንባታ ብረቶችን ከብቁ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የብረት አይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
|
1 |
የድልድይ ብረት ባለ 24 ሚ.ሜትር ሜጋ ፓስካል |
|
|
|
2 |
የድልድይ ብረት ባለ 16 ሚ.ሜትር ሜጋ ፓስካል |
|
|
|
3 |
የድልድይ ብረት ባለ 12 ሚ.ሜትር ሜጋ ፓስካል |
|
|
|
4 |
የድልድይ ብረት ባለ 8 ሚ.ሜትር ሜጋ ፓስካል |
|
|
ስለሆነም አቅራቢዎች፤
- በዘርፉ በ2017 የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን የተጨማሪ እሴት ታከስ ምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- አቅራቢ ድርጅቶች የሚያቀርቡት የድልድይ ብረቶች የጥራት ደረጃቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከዲስትሪክቱ ፋይናንስና ሎጀስቲክስ ስራ ሂደት መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋ 1 /አንድ ፐርሰንት/ በባንኮች የተረጋገጠ ሲፒኦ በማሠራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
- አቅራቢዎች ለእያንዳንዱ ዓይነት ብረት የሚያቀርቡትን ዋጋ የአንድ ቤርጋ ዋጋ ቫትን ያካተተ ሆኖ ዋናውንና ኮፒውን በመለየት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 /አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ ሆሣዕና ዲስትሪክት ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀ ሣጥን መክተት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን ብረቶች ሆሣዕና ዲስትሪከት በማቅረብ የማስረከብ ግዴታ ይኖርበታል፡፡
- የዲስትሪከት ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብት በህግ የተጠበቀ ነው።
የሆሣዕና ዲስትሪክት ጽ/ቤት
